1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰሜን ኮርያ መሪ ሞት

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 3 2004

የሰሜን ኮርያ መሪ ኪም ዦንግ ኢል ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ከመዲናይቱ ፒዮንግያንግ የወጡ ዘገባዎች አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/13S8d
ምስል dapd

የሀገሪቱ ቴሌቪዥን እንዳመለከተው፡ የስድሳ ዘጠኝ ዓመቱ ኪም ዦንግ ኢል የሞቱት ባለፈው ቅዳሜ ጥዋት ሲሆን፡ በባቡር ከመዲናይቱ ወጣ ብለው ወደሚገኝ አካባቢ በመጓዝ ላይ እንዳሉ ነበር ሕይወታቸው ያለፈችው። የልብ ድካም ለኪም ዦንግ ኢል ሞት ምክንያት መሆኑን የቴሌቪዥኑ ዘገባ አክሎ አስታውቋል። የኪም ዦንግ ኢል ዜና ዕረፍት ከተሰማ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ትንሹ የኪም ዦንግ ኢል ልጅ የፓርቲው፡ የጦር ኃይሉ እና የሕዝቡ መሪ በመሆን ሟቹን አባታቸው እንደሚተኩ የሀገሪቱ ይፋ የዜና ወኪል አስታውቋል።

አርያም ተክሌ