1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰማያዊ ፓርቲ የስነ-ሥርዓት ኮሚቴ ቅጣት

ሰኞ፣ መጋቢት 19 2008

የሰማያዊ ፓርቲ የስነ ስርዓት ኮሚቴ በፓርቲው ሊቀመንበር እና በሌሎች ሶስት የአመራር አባላት ላይ የማባረርና የእገዳ ውሳኔ መስጠቱን አሳወቀ ። የፓርቲዉ የስነ ሥርዓት ኮሚቴዉ ያሳለፈውን የቅጣት እና የእገዳ ውሳኔ የፓርቲው ሊቀ መንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት የልጅ ሥራ ሲሉ አጣጣጣሉ።

https://p.dw.com/p/1IKvm
Gambia Street in Addis Abeba, Äthiopien
ምስል picture alliance/dpa

[No title]

ሊቀ መንበሩ እንደሚሉት የስነ ስርዓት ኮሚቴው ርሳቸውን የማባረር ውሳኔ ሊያሳልፍ አይችልም ። ፓርቲያቸው በጉዳዩ ላይ እንደሚነጋገርም ሊቀመንበሩ አስታውቀዋል ። ውሳኔው መተላለፉን ያረጋገጡት የሰማያዊ ፓርቲ የስነ ስርዓት ኮሚቴ ሊቀመንበር ወ/ሮ ሃና ዋለልኝ ዝርዝሩን ከመናገር ግን ተቆጥበዋል ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ