1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሮሂንግያ ሙስሊሞች

ረቡዕ፣ ጳጉሜን 1 2009

በሁለት ሳምንት ውስጥም ከ400 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ህጻናት እና ሴቶች የሚያመዝኑባቸው 125 ሺህ የሚሆኑ ስደተኞች በአስቸጋሪ ሁኔታ ድንበe አቋርጠው ባንግላዴሽ ገብተዋል።

https://p.dw.com/p/2jSu5
Bangladesch Massenflucht der Rohingyas
ምስል picture-alliance/dpa/B. Armangue

የሮሂንግያ ሙስሊሞች

በምያንማር የሮሂንግያ ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ በተከፈተው ግጭት ምክንያት ህዝቡ ለሞት እና ለስደት ተዳርጓል። ከ 2 ሳምንት በፊት አማጽያን በ አንድ የፖሊስ ጣቢያ ላይ ባደረሱት ጥቃት ሰበብ  የማይንማር ወታደሮች በህዝቡ ላይ ጦርነት ከፍተው ጥቃት እያደረሱ መሆኑ እየተዘገበ ነው። በሁለት ሳምንት ውስጥም ከ400 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ህጻናት እና ሴቶች የሚያመዝኑባቸው 125 ሺህ የሚሆኑ ስደተኞች በአስቸጋሪ ሁኔታ ድንበe አቋርጠው ባንግላዴሽ ገብተዋል። በሮሂንግያ ሙስሊሞች ላይ ይሄ ሁሉ በደል የሚፈጸመው የኖቤል የሰላም ተሸላሚ አውን ሳን ሱቺ ሥልጣን ላይ ባሉበት ጊዜ መሆኑ ማነጋገሩ ቀጥሏል።  ገበያው ንጉሴ ዘገባ አዘጋጅቷል