1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የርዕዮት አለሙ የስር ቤት አያያዝ

ማክሰኞ፣ መስከረም 7 2006

የወጣት ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ የእስር ቤት አያያዝ እየተባባሰ እንጂ እየተሻሻለ አለመሆኑ ተሰማ።

https://p.dw.com/p/19jZD
CPJ logo, COMMITTEE TO PROTECT JOURNALISTS, graphic element on white 2008/11/26
Logo CPJምስል APTN

ወላጅ አባቷና ጠበቃዋ እንደሚሉት የጠያቂዎቿ ቁጥር ቀንሷል፣ የእስር ቤት አልጋዋንም ለሌላ እስረኛ እንድትለቅ ተገዳለች። በሌላ በኩል ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማትም ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ያለአንዳንች ቅድመ ሁኔታ እንድትፈታ እየጠየቁ ነው። «ባልፈጸመችው ወንጀል ይልቁንም በመብት ተሙዋጋችነትዋ በእስር ቤት ያውም ኢሰብኣዊ በሆነ አያያዝ እየማቀቀች የምትገነው ወጣት ጋዜጠና ርዕዮት አለሙ» ይላል ዓለም ዓቀፉ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት በምህፃሩ IEWO ባለፈው ዓርብ ባወጣው መግለጫ ለበርካታ ኢትዮጵያት ሴቶችም መልካም አርዓያነት መጠቀስ ከጀመረች ከራርማለች።

ከዚሁ የተነሳ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና ዓለም ዓቀፍ የመብት ተሟጋቾች ሁሉ ይህንኑ በመቃወም ርዕዮት ዓለሙን ጨምሮ ሌሎችም በግፍ ታስረው በእስር ቤት እየተሰቃዩ ናቸው ያላቸው እስረኖች ይፈቱ ዘንድ እንዲተባበሩ ዓለም ዓቀፍ ጥሪ ኣቅርበዋል። ርዕዮት አለሙ በዘመናችን ወደር በሌለው ጀግንነት ከሚወደሱት ጥቂት ኢትዮጵያን መካከል ትጠቀሳለች ያለው ድርጅቱ ለመፃፍ ነፃነቱዋ እና በኣጠቃላይ በመብት ተሟዋጋችነቱዋ በምትከፍለው መስዋትነት ሁሉ ድጋፋችን እንደማይለያት እናረጋግጣለን ብለዋል።

CPJ የተሰነው የጋዜጠኖች መብት ተሟጋች ድርጅትም እንዲሁ የእስር ቤቱ ኣያያዝ እንዲሻሻል ከመጠየቁም ባሻገር ርዕዮት ዓለሙን ጨምሮ እስክንድር ነጋ እና ሌሎችም ያለኣንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ኣሳስበዋል። ያም ሆኖ በእስር ቤቱ የእስረኖች ኣያያዝ እየተባባሰ እንጂ እየተሻሻለ ኣለመሆኑን ነው ዘገባዎች የሚጠቁሙት በተለይም ርእዮት አለሙን የሚጎበኑ ሰዎች ቁጥር መቀነሱን በመቃወም ከመስከረም 1 - 5 ድረስ የረሃብ አድማ ማድረጉዋን ወላጅ አባትዋ እና ጠበቃዋ አቶ ዓለሙ ጎቤቦ ዛሬ ለዶቸቤሌ ኣስረድተዋል።

የጋዜጠና ርዕዮት አለሙ ጤንነት በመልካም ሁኔታ ላይ መሆኑን እና ሞራልዋም ቢሆን ብርቱ መሆኑን የገለጹት አቶ አለሙ የኣመክሮ መብትዋን ተጠቅማ ከወህኒ ቤቱ እንዳትፈታም በለስልጣናቱ ከወዲሁ በሰበብ ኣስባቡ ሴራ እየጠነሰሱ ነው በማለት ይወቅሳሉ።

ጋዜጠና ርዕዮት አለሙ በአወዛጋቢው የጸረ ሽብር ህግ ተከሳ የታሰረችው በሰኔ ወር 2003 ዓ ም ሲሆን በተያዘባት የወንጀል ጭብጥ የ14 ዓመት እስራት ከተበየነባት በሁዋላ በይግባን ወደ 5 ዓመት ዝቅ ብሎላታል ከዚህ ሁሉ ሂደት ጋርም ጋዜጠና ርእዮት ዓለሙ ባለፈው ዓመት የ2013 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠና ተብላ በ ዓለም ዓቀፉ የትምህርት እና የባህል ተቐም UNESCO ኣማካንነት ዓለም ዓቀፍ የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ማሸነፍዋ ይታወሳል።

ጃፈር አሊ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ