1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሪዮ ኦሊምፒክ እና የአትሌቶች ቅሬታ

Merga Yonas Bulaሐሙስ፣ ግንቦት 25 2008

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና ሌሎች ወደ አራት የሚጠጉ አትሌቶች በብራዚል ሪዮ ዴ ጃኔሪዮ በሚካሄደዉ ዓለም አቀፍ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ኢትዮጵያን ወክለው እንዲወዳደሩ ከተመረጡት መካከል አለመሆናቸውን የኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌዴሬሸን ሰሞኑን ይፋ አድርጓል።

https://p.dw.com/p/1IzQG
Weltmeisterschaften Leichtathletik 10000 Meter Lauf Finale
ምስል AP

[No title]

ብራዚል ከሁለት ወር በኋላ ፊታችን ነሀሴ በሪዮ ዴ ጃኔሪዮ የሚካሄደውን የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ውድድር ለማስተናገድ ደፋ ቀና እያለች ትገኛለች። አትሌትክስ አንዱ የዉድድሩ አካል ሲሆን፣ በዚሁ ጨዋታ ከ10,000 በላይ አትሌቶች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቁ ከአዘጋጅው ድረ ገፅ መረዳት ተችለዋል።

በሩጫ ዉድድር ብዙ አትሌቶችን ለማሳተፍ ከወራት በፊት ጀምሮ ዝግጅት የጀመረው የኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌዴሬሸንም ፣ በተለያዩ የሩጫ ውድድር የሚሳተፉ አትሌቶችን ቀደም ብሎ ሲመርጥ፣ በማራቶን የሚሳተፉትን አትሌቶች ያሳወቀው ዘግየት ብሎ ነበር። ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት እንደሚናገሩት፣ የኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌዴሬሸን የማራቶን ተሳታፊዎችን ለመምረጥ የተጠቀመበት አዲስ መስፈርት እና በዚሁ መሰረት በደረሰው ውሳኔው አንጋፋ የተባሉት አትሌቶች ከተሳታፊዎቹ መካከል አለመካተታቸው ሰሞኑን ብዙ እያነጋገረ ነው።

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ጨምሮ ሌሎች አራት አትሌቶች በዉድድሩ ላይ አለመሳተፋቸዉ በርካታ ጥያቄዎችን እንዳስነሳ እና የወጣዉ መስፈርት <<በጣም የዘገየ፣ ህግ ያልተከተለ፣ አሻሚ እና አወዛጋቢ>> መሆኑን የስፖርት ጋዚጤኛ ምስጋናዉ ታደሰ ለዶይቸ ቬሌ ተናግሮዋል።

ፌደሬሸኑ በአዲሱ መስፈርት ላይ አትሌቶቹን ሳያወያይ ውሳኔውን እራሱ መድረሱ አትሌቶቹን እና ህዝቡን ቅር እንዳሰኘ ጋዜጠኛው አስረድቶዋል። የፌዴሬሸኑን ርምጃን ተከትሎ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ መስፈርቱን እንደሚያሟላ ተናግሮ መራጩ ኮሚቴ ግልፅነት የጎደለዉ፣ አድሎ የታየበት እና የወጣዉ መስፈርት በድብቅ ነዉ በማለት ውሳኔውን ተችቶዋል። መስፈርቱ መዉጣቱ የተወሰነ ግለሰቦችን ለመጥቀም መሆኑን ቀነኒሳ ተናግሮ ባጠቃላይ የሚታየዉ ነገር <<ደስ>> እንዳላሰኘው ገልጾዋል።

Kenenisa Bekele
ምስል AP Photo/Mark Baker

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ