1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀድሞ የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚደንት ሪየክ ማቸር ከሀገር መሸሽ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 12 2008

የቀድሞ የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት እና የተቃዋሚው የ«ኤስ ፒ ኤል ኤ - አይ ኦ» መሪ ሪየክ ማቸር ሀገራቸውን ለቀው ወደ ጎረቤት ሀገር መሸሻቸውን የ«ኤስ ፒ ኤል ኤ -አይ ኦ» ቃል አቀባይ ጋትዴት ዳክ ገለጹ።

https://p.dw.com/p/1Jl89
Südsudan Riek Machar Rebellenführer
ምስል picture-alliance/AP Photo/M. Ayene

[No title]

ካለፈው ሚያዝያ እስካለፈው ሀምሌ ወር አጋማሽ የሽግግሩ መንግሥት ምክትል ፕሬዚደንት ሆነው የሰሩት ማቸር የሸሹት ከተቀናቃኞቻቸው የደቡብ ሱዳን መንግሥት ጦር ክትትል ስላረፈባቸው መሆኑን ቃል አቀባዩ አመልክተዋል። ማቻር በአሁኑ ጊዜ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሬፐብሊክ መዲና ኪንሻሳ መግባታቸውንም ቃል አቀባዩ አክለው አስታውቀዋል። የሪየክ ማቸር ከደቡብ ሱዳን መሸሽ በሀገሪቱ ጊዚያዊ ሁኔታ ላይ ምን አንደምታ ይኖረዋል? የናይሮቢ ወኪላችንን ፋሲል ግርማን አነጋግሬዋለሁ።

ፋሲል ግርማ

አርይም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ