1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሩዋንዳው የስለላ ኃላፊ በብሪታንያ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 5 2007

ኢማኑኤል ካሬንዚ በዋስ ከተፈቱ በኋላ ከለንደን ሳይወጡ ምርመራ እየተደረገባቸው ከቆየ በኋላ ትናንት የእንግሊዝ ፍርድ ቤት ለስጳኝ አሳልፎ እንደማይሰጣቸው ውሳኔ አስተላልፏል። ኢማኑኤል ካሬንዚን የእንግሊዝ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ለምን ነበር?

https://p.dw.com/p/1GDZa
Ruanda Sicherheitschef Karenzi Karake
ምስል J. Tallis/AFP/Getty Images

[No title]

የርዋንዳ ብሔራዊ የስለላ እና ፀጥታ ዋና ኃላፊ የ54 ዓመቱ ኢማኑኤል ካሬንዚ ካራኬ ባለፈው ሰኔ ወር ለሥራ ጉዳይ ወደ እንግሊዝ አቅንተው ለንደን አየር ማረፊያ ላይ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው ነበር። የእንግሊዝ ፖሊስ ኃላፊውን በቁጥጥር ስር ያዋለው በስጳኝ ፍርድ ቤት ጥያቄ ነበር። ኢማኑኤል ካሬንዚ በዋስ ከተፈቱ በኋላ ከለንደን ሳይወጡ ምርመራ እየተደረገባቸው ከቆየ በኋላ ትናንት የእንግሊዝ ፍርድ ቤት ለስጳኝ አሳልፎ እንደማይሰጣቸው ውሳኔ አስተላልፏል። ኢማኑኤል ካሬንዚን የእንግሊዝ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ለምን ነበር? ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ለለንደኑ ወኪላችን ድልነሳው ጌታነህ ያቀረብኩለት የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር።

ድልነሳው ጌታነህ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ