1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የረሃብ ስጋት በደቡባዊ አፍሪቃ ሃገራት

ዓርብ፣ ጥር 27 2008

በኢትዮጵያ ኤል-ኒኖ የደቀነዉ የድርቅ ችግር፤ በአስር የደቡባዊ አፍሪቃ ሃገራትም የረሃብ ስጋት ማስከተሉን የተመ የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታዉቋል።

https://p.dw.com/p/1HqZ5
Düre in Nordkorea
ምስል picture alliance / dpa


የዚምባብዌዉ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በሃገራቸዉ ገጠራማ አካባቢዎች በተከሰተዉ ድርቅ ምክንያት የአስቸኳይ አደጋ ጊዜ አዋጅ ደንግገዋል። ሙጋቤ ይህን አዋጅ ይፋ ለማድረግ የተገደዱት የአዉሮጳ ኅብረት ረሃብ የተደቀነበትን የዚምባቡዌን ሕዝብ ለመርዳት ድርጅቶች ገንዘብ ማሰባሰብ የሚችሉት አደጋዉ በይፋ ሲነገር መሆኑን ለፕሬዚዳንቱ ማሳሰባቸዉን ተከትሎ መሆኑ ነዉ የተመለከተዉ። የመንግሥታቱ ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዚምባብዌ፤ ማዳጋስካርና ሌሴቶን ጨምሮ 10 ደቡባዊ አፍሪቃ ሃገራት የረሃብ አደጋ መከሰቱን መግለፁ ይታወቃል። በዚምባቤ 2,4 ሚሊዮን ነዋሪ ብሎም በሌሎች የደቡባዊ አፍሪቃ ሃገራት ለረሃብ አደጋ መጋለጣቸዉን በተመለከተ ናይሮቢ ኬንያ የሚገኘዉን ወኪላችንን አነጋግረነዉ ነበር።

ፋሲል ግርማ

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ