1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሞቃዲሾዉ አጥፍቶ ጠፊ

ዓርብ፣ ሐምሌ 24 2007

የ29ኝ ዓመቱ ወጣት ከዚሕ ቀደም ወደ ኢራቅ ወይም ሶሪያ ለመጓዝ ሲሞክር ተይዞ ታስሮም እንደነበር ዘገቦች ይጠቁማሉ።ወጣቱ ባፈነዳዉ ቦምብ አስራ-ሰባት ሰዎች አጥፍቶ ሲጠፋ ሌሎች አስር አቁስሏል

https://p.dw.com/p/1G81I
ምስል Reuters/F. Omar

[No title]

ባለፈዉ ዕሁድ ሶማሊያ ርዕሠ-ከተማ ሞቃዲሾ ዉስጥ አንድ ሆቴል ደጃፍ በመኪና ላይ የጫነዉን ቦምብ ያፈነዳዉ አጥፍቶ ጠፊ ሊቢያ ተወልዶ፤እዚሕ ቦን-ጀርመን ኖሮ ወደ ሶማሊያ የሔደ ወጣት እንደነበር የጀርመን የፀጥታ ባለሥልጣናትና መገናኛ ዘዴዎች አስታወቀዋል።የ29ኝ ዓመቱ ወጣት ከዚሕ ቀደም ወደ ኢራቅ ወይም ሶሪያ ለመጓዝ ሲሞክር ተይዞ ታስሮም እንደነበር ዘገቦች ይጠቁማሉ።ወጣቱ ባፈነዳዉ ቦምብ አስራ-ሰባት ሰዎች አጥፍቶ ሲጠፋ ሌሎች አስር አቁስሏል።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ