1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምግብ ሳይንስ ባለሞያው ዶክተር አየለ ጉግሳ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 26 2006

የነፃ ትምህርት እድል አግኝተው በመጡባት ጀርመን ሲኖሩ ከ27 ዓመት በላይ ሆኗቸዋል ። የግብርና ውጤቶችን የምግብ ይዘትና ጠባይ አጥንቶ ለምግብነት ማዘጋጀት የሚያስችል ትምህርት ነው ያጠኑት ። የተማሩትም በበርሊኖቹ አሌክሳንደር ሁምቦልትና የቴክኒክ ዩኒቨርስቲዎች ነው ። ዶክተር አየለ ጉግሳ ይባላሉ

https://p.dw.com/p/1ACLg
ምስል picture-alliance/dpa

የማስትሬት ዲግሪያቸውን ከአሌክሳንደር ሁምቦልት ዩኒቨርስቲ ካገኙ በኋላ የዶክትሬት ዲግሪያቸው እዚያው ማጥናት ቀጥለው ሁለቱ ጀርመኖች ሲዋሃዱ ዩኒቨርስቲው የሚያጠኑትን ትምህርት መስጠት በማቋረጡ ወደ በርሊኑ የቴክኒክ ዩኒቨርስቲ ተዛውረው ትምህርታቸውን ለማጠናቀቅ በቅተዋል ። የዶክተር አየለ የማስትሬትና የዶክትሬት ዲግሪዎቻቸው የመመረቂያ ሥራዎች በተመሳሳይ መስክ ላይ ያተኮሩ ናቸው ።ዶክተር አየለ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ባገኙበት በበርሊኑ የቴክኒክ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ለአራት ዓመታት በጥናትና ምርምር ሠርተዋል ። ከዚያ በኋላም በአንድ የዱቄት ፋብሪካ ውስጥ ተቀጥረው ያገለግሉም ነበር ። ለአምስት ዓመታት በዚሁ ፋብሪካ ውስጥ ያገለገሉት ዶክተር አየለ ከሁለት ዓመት ግድም ወዲህ ደግሞ በሙያቸው በግል ሥራ ላይ ይገኛሉ ። እውቀታቸውን ወደ ኢትዮጵያ በማሸጋገርም እየሰሩ ነው ። በዶክተር አየለ እምነት ኢትዮጵያን በመሰለች ሃገር ምግብ ማምረት አስቸጋሪ ባልሆነም ነበር ። ይሁንና በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሃገሪቱ ከምግብ እጥረት ልትላቀቅ አልቻለችም ። ለዶክተር አየለ በኢትዮጵያ የምግብ እጥረት ሁለት ገፅታ አለው ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ