1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምክር ቤት ምርጫ በእሥራኤል

ማክሰኞ፣ መጋቢት 8 2007

በእሥራኤል 120 መቀመጫዎች ላሉት 20ኛው የክኔሴት ማለትም የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ምርጫ በመኪያሄድ ላይ ነው። 5.8 ሚሊዮን ነዋሪዎች ለመምረጥ መመዝገባቸው ተጠቅሷል። የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት እኩለ ሌሊት ላይ የሚገለጥ መሆኑም ተነግሯል።

https://p.dw.com/p/1EsHh
Israel Wahlen 2015
ምስል Reuters/Uri Lenz

የሕዝብ አስተያየት መለኪያዎች ማጠቃለያ እንዳመለከተው ከሆነ ተቃዋሚው የጽዮናውያን ኅብረት ከአራት መቀመጫዎች ሦስቱን በማግኘት ከገዢው ሊኩድ ፓርቲ እንደሚልቅ ተተንብዮዋል። የሊኩድ ፓርቲ መሪው ጠቅላይ ሚንሥትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ከወዲሁ ስጋት የገባቸው ይመስላል። ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት የእሥራኤሉ ወኪላችን ጋዜጠኛና ደራሲ ዜናነህ መኮንንን አነጋግሬዋለሁ። መራጩ ሕዝብ በአብዛኛው የኢኮኖሚ ጥያቄ ቢያቀርብም ፖለቲከኞች ግን ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረጋቸውን ዜናነህ ጠቅሷል። የእስራኤል ምርጫን በተመለከተ የመገናኛ ብዙኃን እና የኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤላውያንን ጨምሮ የሕዝቡ አስተያየት ብሎም ሚናው ምን እንደሚመስል በማብራራት ይጀምራል።

ዜናነህ መኮንንን

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ