1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምሥራቅ ወለጋው ኪራሙ ወረዳ ተጎጂዎች ሁኔታ

ዓርብ፣ ነሐሴ 21 2013

ነሐሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም. በምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ በዋናነት የአማራ ተወላጆችን ኢላማ አድርጎ በታጣቂዎች ተፈጽሟል በተባለ ጥቃት የተጎዱትን ወደ ተረጋጋ ሁኔታ ለመመለስ የፀጥታ ኃይሎችን ወደ ስፍራው ማሰማራቱን የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ። ክልሉ የአደጋ መንስኤ እና መጠኑን የሚያጣራ ልዑክ አደራጅቶ ወደ ስፍራው መላኩን አስታውቋል፡፡

https://p.dw.com/p/3za89
Äthiopien | Getachew Balcha
ምስል Seyum Getu/DW

የምስራቅ ወለጋው ኪራሙ ወረዳ ተጎጂዎች ሁኔታ

ነሐሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም. በምሰድራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ በዋናነት የአማራ ተወላጆችን ኢላማ አድርጎ በታጣቂዎች ተፈጽሟል በተባለ ጥቃት የተጎዱትን ወደ ተረጋጋ ሁኔታ ለመመለስ የፀጥታ ሃይሎችን ወደ ስፍራው ማሰማራቱን የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ። ክልሉ የአደጋ መንስኤ እና መጠኑን የሚያጣራ ልዑክ አደራጅቶ ወደ ስፍራው መላኩን አስታውቋል፡፡
ክፍተቱ እንዲፈጠር አስተዋፅኦ ያደረገ አመራርም ሆነ የትኛውም አካል ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ያለው ክልሉ የነዋሪዎቹን ዘለቀታዊ ሰላም ለማረጋገጥም እንደሚሰራ ነው ያመለከተው። 

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮምያ ክልል፣ ምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ ኪራሙ ወረዳ ነሃሴ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. በአካባቢው ተሰማርተው የነበሩ የፀጥታ ኃይሎች ወደ ሌላ አካባቢ መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ፣ ነሐሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም. የ«ኦነግ ሸኔ» ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች ብሔርን መሰረት አድርጎ አድርሷል ባለው አሳሳቢ ጥቃት ከ150 በላይ ነዋሪዎች መገደላቸውን ትናንት ባወጣው መግለጫ አስረድተዋል። ኢሰመኮ በመግለጫው ጥቃቱን ተከትሎ ከታጠቂው ወገን በተውጣጡ ሰዎች በተወሰደው ብሔርን መሰረት ያደረገ የአፀፋ እርምጃ ከሌላው ወገን 60 ሰዎች በመገደላቸው በርካታ ነዋሪዎች ተፈናቅለው ወደ ኪራሙ ከተማ እና አማራ ክልል ሸሽተዋል።

ስዩም ጌቱ

እሸቴ በቀለ 
ሸዋዬ ለገሠ