1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምሥራቅ ኮንጎ አማጽያን ግሥጋሤ

ረቡዕ፣ ኅዳር 12 2005

ጎማ ውስጥ በሺ የሚቆጠሩ የመንግሥት ወታደሮችና የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ኃይሎች እንደሚገኙ የታወቀ ሲሆን ፤ የጎማ መያዝ በፕሬዚዳንት ጆሰፍ ካቢላ ለሚመራው የኪንሻሳ አስተዳደር እንደ አንድ ድቀት ነው የሚታየው።ጎማ ከተያዘች በኋላ በአገሪቱ በመላ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል ።

https://p.dw.com/p/16nkm
REFILE - ADDING LOCATION WHERE PICTURE WAS TAKEN Displaced people cross the border from the Democratic Republic of Congo (DRC) into Rwanda, as seen from Gisenyi, November 20, 2012, as the Congolese Revolutionary Army fights with the DRC government army on the periphery of Goma, the capital of Congo's North Kivu province. Rwanda accused U.N.-backed Congolese forces of shelling its territory during a battle with rebels near the border on Monday but said it had no plans to respond militarily to what it called Kinshasa's "provocation". REUTERS/James Akena (RWANDA - Tags: CIVIL UNREST POLITICS) // eingestellt von se
ምስል Reuters
Congolese Revolution Army (CRA) rebels stand guard at the border entry into Rwanda near Goma in the eastern Democratic Republic of Congo (DRC), November 20, 2012, soon after the rebels captured the city from the government army. Rebels widely believed to be backed by Rwanda claimed control of Goma in the eastern Democratic Republic of Congo on Tuesday, walking through the frontier city of one million people past U.N. peacekeepers who did nothing to stop them. REUTERS/James Akena (DEMOCRATIC REPUBLIC OF CONGO - Tags: CIVIL UNREST POLITICS) // eingestellt von se
ምስል Reuters

M 23 በሚል መጠሪያ የታውቁት የምሥራቅ ኮንጎ አማጽያን፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኑዋሪዎች ያሏትን የክፍለ ሀገሩን ርእሰ ከተማ ጎማን በቁጥጥራቸው ሥር አውለዋል። ለወራት ያህል ይህን እንደሚያደርጉ የዛቱት አማጽያን፤ በ 4 ቀናት የተፋፋመ ውጊያ ነው ከተማይቱን ለመያዝ የቻሉት። ጎማ ውስጥ በሺ የሚቆጠሩ የመንግሥት ወታደሮችና የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ኃይሎች እንደሚገኙ የታወቀ ሲሆን ፤ የጎማ መያዝ በፕሬዚዳንት ጆሰፍ ካቢላ ለሚመራው የኪንሻሳ አስተዳደር እንደ አንድ ድቀት ነው የሚታየው። ጎማ ከተያዘች በኋላ በአገሪቱ በመላ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል ። ስለአማጽያኑ ግሥጋሴና የጎማ ይዞታ የዶቸ ቨለ የአፍሪቃው ክፍል ባልደረባ ዚሞነ ሽሊንድቫይን ያቀረበችውን ዘገባ ተክሌ የኋላ እንደሚከተለው አቀናብሮታል።

የዩጋንዳ፣ ኮንጎና ሩዋንዳ መሪዎች ፤ የምሥራዊቷን ኮንጎ ርእሰ-ከተማ ጎማን፣ በአማጽያን መያዝ አስመልክተው ካምፓላ ውስጥ መክረዋል። ውዝግቡ ይበልጥ እንዳይስፋፋ ሥጋት አለ። በጎማ መዳረሻ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች በሚገኙበት ማዕከል የኑዋሪዎች አሳዛኝ ጉስቁልና እንደሚታይ ተመልክቷል። 500 ያህል እናቶች በዛ ያሉ ጨቅላዎች፤ በአሸዋ በተሞሉ ዶንያዎች በታጠረ ሥፍራ ተኮልኩለው ይገኛሉ። በተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪዎች ሠፈር የደኅንነት ዋስትና ይኖራል ብለው በማሰብ ከባልተቤታቸውና 6 ልጆቻቸው ጋር የተጠለሉት Antoine Bwenge -«ምግብና መድኃኒት የለም። የኅጻናቱ ይዞታ ሥጋት ላይ ጥሎናል። ካለፈው እሁድ አንስቶ እህል አልቀመሱም። ትናንት ማታ አማጽያኑ ወደ ከተማይቱ ሲጠጉ ፣ ከመንግሥት ወታደሮች ጋር በተደረገው ፍልሚያ፣ ጥይቱ በላያችን ላይ ሲያፏጭ መድፉም ሲያጓራ ነበረ። ሽብር በሽብር ነበረ የሆነው። ሌሊቱን ሜዳ ላይ ነው ያነጋነው። ሁኔታው እጅግ አስከፊ ነው።»
ዓለም አቀፉ የውዝግቦች አጥኚና ተንታኝ ድርጅት (ICG)ትናንት ከለንደን እናዳስታወቀው ከሆነ የጎማ በአማጽያን መያዝ ፣ በኮንጎና በሩዋንዳ መካከል ጦርነት እንዳያስነሳ ያሠጋል። ዩጋንዳ ፣ ማዕራባዊውን ወሰኗን በጥብቅ ከመቆጣጠሯም ሌላ፤ ውጊያው ከድንበሯ እንዳያልፍ ዋናውን የወሰን ጎዳና ባለፈው ሳምንት መዝጋቷ የሚታወስ ነው። ሩዋንዳና ዩጋንዳ፤ ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መርማሪና ብይን ሰጪ ፍርድ ቤት በወንጀል የሚፈልጋቸው የጦር ሠራዊት ጀኔራል ቦስኮ እንታንጋንዳ የሚመሩትን የአማጽያን ቡድን ነው የሚደግፉ በማለት ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ የሠነዘረችውን ክስ ሐሰት ሲሉ አስተባብለዋል።


የምሥራቅ ኮንጎ አማጽያን ጎማን በዛሬው ዕለት ሲቆጣጠሩ ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የመንግሥት ወታደሮችና ፖሊሶች፤ እየከዱ ከእነርሱ ጋር መቀላቀላቸው የታወቀ ሲሆን፤ እነዚሁ M 23 በመባል የታወቁት አማጽያንም ፤ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክን በመላ«ነጻ እናወጣለን » የሚል ዛቻም ሆነ መግለጫ በማሰማት ላይ ናቸው። በሺ የሚቆጠሩ የጎማ ኑዋሪዎች፤ በ M 23 ኮሎኔል ቪያኒ ካዛራማ መግለጫው ሲሰጥ ደስታቸውን በጭብጨባ መግለጣቸው ነው የተነገረው። ካዛራማ፤ የደቡብ ኪቩ ጠ/ግዛት ርእሰ ከተማ ቡካቩ ቀጣይ ዒላማ መደረጓን አያይዘው ነው የገለጡት። ህዝቡም ሰላምና ፀጥታ እስከምን ድረስ እንደሚሠፍኑ ሳያውቅ በመፈንጠዝ ላይ ነው።
በጎማ መያዝ ሁሉም አይደለም የተደሰተው የተናደዱ ፣ ብርቱ ቅሬታ ያደረባቸው ጥቂቶች አይደሉም።
«መንግሥታችን አሳልፎ እንደሰጠን ነው የሚሰማን። ምን እንደምናደርግ ግራ ገብቶናል። የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች፤ ሰላም እንደሌለ እያወቁ ሁሉንም ነገር ችላ ብለውታል። ምንም ሳይከላከሉ ነው አማጽያኑ ጎማን ገብተው የያዟት። እንደተታለልን ነው የሚሰማን!»

The M23 rebels spokesperson Vianney Kazarama (L) speaks to the crowd who have gathered at a stadium in Goma November 21, 2012. Rebel forces in eastern Congo said on Wednesday they planned to take control of the whole of the vast central African country after they captured the eastern town of Goma while United Nations peacekeepers looked on. REUTERS/James Akena (DEMOCRATIC REPUBLIC OF CONGO - Tags: CIVIL UNREST POLITICS)
ምስል Reuters

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ