1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማንበብ ባህል በኢትዮጽያ

እሑድ፣ ጥቅምት 29 2002

በዚህ በለጸጉ በሚባሉት በአዉሮጻዉያኑ አገር የማንበብ ባህል በትክክል በህብረተሰቡ ዉስጥ ይታያል። ንባብ ለግዜ ማሳለፍያ፣ ለመዝናኛ፣ እንዲሁም ለዕዉቀት መግብያ ሲሆን ከልጅ እስከ አዋቂ ሲገለገልበት ይታያል።

https://p.dw.com/p/KQj5
ምስል picture alliance/dpa

እንደዉም አብዛኞች በትዉዉቃቸዉ ምን አይነት መጽሃፍ ማንበብ እንደሚወድ፣ እንደምትወድ እንዲሁም ምን ዝንባሌ ወይም ለምን ነገር ልዩ ፍቅር እንዳለዉ እንዳላት ይጠያየቃሉ። በአገራችንስ የማንበብ ባህል አለን? ካለስ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ይህንን ጥያቄ ይዘን ወደ አገር ቤት ምሁራን ማፈላለግ ጀመርን፣ ያገኘናቸዉ ምሁር ታድያ በአገራችን የማንበብን ባህል ጥንታዊነት ገለጹልን። እንደዉም መጸሃፍን የሚያነብ ሰዉ መጽሃፍ ገላጭ ይባል ነበር አሉን! በጥንት ግዜ፣ በቤተ ክህነትም፣ በትክክል ተማሪዉ እንዲማር እና እንዲያነብ ከመጠምጠም መማር ይቅደም ሲባል ይገጸስ ነበር አሉን። የቀለም ቀንድ ማለት ምን ትርጉም እንዳለዉ ያዉቃሉ? አድማጮች ለሁሉም የዛሪዉ መድረካችን ሁለት ምሁራንን ይዞ በአገራችን ስላለዉ የማንበብ ባህል ሊያስቃኘን ተዘጋጅቶአል ለጥንቅሩ አዜብ ታደሰ ነኝ መልካም ቆይታ

አዜብ ታደሰ