1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

ሰኞ፣ መጋቢት 23 2011

እኛ የፖለቲካ ፓርቲ አይደለንም። የፖለቲካ ሥልጣንም አንፈልግም። ዋና ተግባራችን ለሚቀጥለው ምርጫ በአዲስ አበባ ዙሪያ ጥሩ አቋም እና የነዋሪዎቿን መብት ያስጠብቃል ያልነውን ፓርቲ ህዝቡ እንዲመርጠው ግፊት ማድረግ ነው።

https://p.dw.com/p/3Fu3e
Äthiopien Addis Abeba
ምስል DW/S. Muchie

በአዲስ አበባ ዙሪያ ጥሩ አቋም እና የነዋሪዎቿን መብት ያስጠብቃል

 

ሰሞኑን ኢትዮጵያዉያን በማኅበራዊ መገናኛዎች በስፋት ከተነጋገሩባቸዉ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት  ፤ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ጋዜጠኛና ከሰብዓዊ መብት ተሟጋት እስክንድር ነጋ፤  እና ፕሮፊሰር ብርሃኑ ነጋ ፤ በአዲስ አበባ በቅርስ የተመዘገቡ ጥንታዊ መኖርያ ቤቶች በቡልዶዘር መፍረስ የሰጡት አስተያየት በርካቶችን አስተያየት አወራዉሮአል።

አዲስ አበባን በተመለከተ አቋማችን ከጋዜጠኛ እና ከሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ ጋር ተመሳሳይ ነው ለማለት ያህል ነው። ማንኛውም የከተማዋ ነዋሪ በህጋዊ መንገድ ለመደራጀት የሚያደርገውን ጥረት እደግፋለሁ!  አዲስ_አበባ  ይድነቃቸዉ መኮንን በፊስ ቡክ ያስቀመጡት አስተያየት ነዉ።  ሰሞኑን በተለይ መገናኛ ብዙኃን ሲቀባበለዉ የነበረዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ንግግር ነበር። ግልጽ ደብዳቤለክቡር ጠ/ሚንስትር ዶር ዐብይ አህመድ – በአሜሪካ ከምንገኝ ተቆርቋሪ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሲሉ 42 ኢትዮጵያዉያን መልክት አስተላለፉ።  

Eskinder Nega - Äthiopien Journalist & Menschenrechtsaktivist
ምስል B. Manaye

« በእስክንድር ነጋ ላይ የሚካሄደው ማስፈራራትና አላስፈላጊ ዛቻና በአስቸኳይ እንዲቆምና በዚህ የታወቀና ጨዋ ኢትዮጵያዊ ላይ አደጋ እንዳይደርስበት ትኩረት እንዲሰጡልን ድምጻችን ለማሰማት ነው።» ይላል በጣም ከብዙ ባጭሩ የደብዳቤዉ መልክት ይዘት ። ለዚሁ ደብዳቤ በዚሁ የመገናኛ ብዙኃን አንድ መልስ ደርሶአል።

«ይድረስ ለ 42ቱ ዳያስፖራ ኣቤቱታ እቅራቢዎች ግልፅ ደብዳቤ» በሚል ርዕስ። ለ ዶክተር እቢይ የላካችሁትን ደብዳቤ እየሁት፤ እስክንድር በረጅሙ የትግል ዘመኑ ትልቅ ቦታ የደረሰና ከባድ ውለታ የዋለልን ለመሆኑ ማንም የሚያውቀው ሃቅነው፤፤ ያ ትላንት ነው፤፤ ዛሬን ላይ ቆመን ስናስተውል ግን  ህግን ጥሶ ተፃራሪ መንግስት ለመፍጠር መከጀልና ማቀድ በጭራሽ እይቻለውም፤፤ ይህን መዋጥ የግድ ይላል እየመረረም ቢሆን፤፤ የሚገርመኝ የሱ ህገወጥነት ሳይሆን የናንተው ምልጃ ነው፤ የ 100 ሚሊዮን ህዝብ መከራና እበሳ መሸከሙ ሳያንሳቸው ለእስክንድርም ህይወት ዋስትና እንዲሰጣችሁም ጠይቃችሁዋል፡፡» ይላል

ነፃነት ኪዳኔ የተባሉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚ ባስቀመጡት አስተያየት ደግሞ እስክንድር ትናንት አባቶችህንም በብእሩ ነው ያስቀዘናቸው። አሁንም በሀሳብ ልዕልና እንጂ ወጣቶችን ወደ አላስፈላጊ ረብሻ የሚነዳ መደዴ አይደለም።»

ይፋታኤል አቤል የተባሉ ተጠቃሚ በበኩላቸዉ « በአደባባይ ገጀራ ይዞ የወጣን ቄሮ ዝም ብሉ። በስላማዊ መንገድ የሚታገለውን የአዲስ አበባ ህዝብን እና እስክንድርን ለማስፍራራት መሞከር ከአብይ አይጠበቅም። ያሳፍራል ያን ሁሉ ግዜ እንዳልደገፍነው።» ሲሉ አስተያየታቸዉን አስቀምጠዋል።

« ዶ/ር አብይ ባላደራ የተባለው ባልደራስ ከመሰብሰብ ውጭ ምን ችግር ፈጥሮ ነው እንደዚህ አይነት ጨዋታ አንፈልግም የተባለዉ? ሀሳብን መግለፅ ለማን ተችሎ ለማን ነው የማይቻለው? የለገጣሮ ቤት ሲፈርስ ያልሰማ ሰው፤ አንድ አዳራሽ ውስጥ የነበረን ተሰብሳቢ እንዴት ተማህ? ቦሌ ላይ ግጭት ለመፍጠር የሞከሩትን ለምን ማስጠንቀቂያ አልሰጡም፡፡ ለምን ሰው ገድሉ ከነመኪናቸው የሚያቃጥሉትን አላስጠነቀቁም? 17 ባንክ ሲዘረፋስ? ድንጋይ፡ ሜንጫና ሚስማር በሀገሪቱ መዲናና ከተሞች ይዞ የሚወጣውን ለማስንጠንቀቅ ለምን ዳር ዳር ተባለ፡፡ አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ ነው ወይስ አይጥ ለሞቷ የድመት አፋንጫ ታሸታለች ነው፡፡» ማይ ኢትዮጵያ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ አስተያየታቸዉን አስቀምጠዋል።

ጃሳ ኖሚና የተባሉ ተከታታይ በበኩላቸዉ «አብይ በየዕለቱ የሚወገዘው ፡ የሚሰደበው በእርግጥም እስከዛሬ ከነበሩት የተሻለ መሪ ሰለሆነ ነው፡፡ የመናገር የመፃፍ የመደራጀት ነፃነት በር ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ስለከፈተ ነው፡፡ ዛሬ ያገኘነው ነፃነት እስከ ዛሬ ያላየነውና ያልለመድነው ሆኖ ነው አብይን ደካማ መሪ ያሰመሠለብን፡፡» ብለዋል።

Äthiopien Diskussion zwischen den PM Abiy Ahmed und Opposition
ምስል DW/Y.-G. Egiziabher

 

የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሚመራውን የአዲስ አበባ ሕዝብን ድምጽ ለማሰማት የሚንቀሳቀሰውን ባላደራ ትክክል አለመሆኑን በገዢው ኦሮሞ ብሮድካስቲን ኔትወርክ (OBN) ቀርበው ለሰጡት ቃለ መጠይቅ <<ባለአደራ ምናምን የሚባለው ነገር ለኔ ትክክል አይመስለኝም። አቶ ታከለ ይሄን የማሸጋገር ሂደት በሚመለከት በትክክል ያልሰራው ነገር አለ ከተባለ ሂስ ማቅረብ ጥሩ ነው።>> አሉ ማለታቸዉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን የተለያየ አስተያየት አወራዉሮታል።

ሄለን ጉግሳ የተባሉ የፌስ ቡክ ተከታታይ፤ « ምነዉ ይን ያህል በባላደራ ኮሚቴ ስታስፈራራ ለባለሜጫዉና ኮንዶሚኒየም ለመዝፍ ለቋመጠዉና ገጀራና እንጨትላይ ሚስማር አሰክቶ ለሚስፈራራዉ ጋጨወጡ ጃዋር አንዲት ቃል ማስጠን ቀቂያ አጣህለት? እረተዉ አንተዛዘብ? እስክንድርኮ ምርጥ የህዝብ ልጅነዉ አቶመለስም ቀብራቸዉ የፈጠዉ የማይነካዉን የንብ ቀፎ የነኩለት ነዉ:: ዶ/ር አብይ ይልቁኑ ቆምብ አሱቦ መነጋገሩ ጠቃሚ ነዉ::ያለዛ ፍፃሜዉ አያምርም:» አክቲቪስትና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በበኩሉ ፤ "እኛ የፖለቲካ ፓርቲ አይደለንም። የፖለቲካ ሥልጣንም አንፈልግም። ዋና ተግባራችን ለሚቀጥለው ምርጫ በአዲስ አበባ ዙሪያ ጥሩ አቋም እና የነዋሪዎቿን መብት ያስጠብቃል ያልነውን ፓርቲ ህዝቡ እንዲመርጠው ግፊት ማድረግ ነው።" ማሉትን የፌስቡክ ተከታታዮች ሲያሰራጩት የነበረ መረጃ ነዉ። ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ! 

 

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሠ