1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማሌዥያ የመንገደኞች አዉሮፕላን ጋየ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 10 2006

አዉሮፕላኑ አሳፍሯቸዉ የነበሩ ሁለት መቶ ሰማንያ መንገደኞችና አሥራ-አምስት ሠራተኞቹ በሙሉ አልቀዋል።

https://p.dw.com/p/1Cek6
Absturzstelle Malaysia Airlines MH-17 Ukraine
ምስል Reuters

በርካት መንገደኞችን አሳፍሮ ከአምስተርዳም-ኔዘርላንድስ ወደ ኩዋላላፑር-ማሌዢያ ይበር የነበረ የማሌዢያ አዉሮፕላን ምሥራቃዊ ዩክሬን ሲደርስ ወድቆ ተከሰከሠ።የሩሲያ ዜና አገልግሎት ኢንትርፋክስ እንደዘገበዉ አዉሮፕላኑ ሩሲያ ግዛት ሊገባ ጥቂት ሲቀረዉ ነዉ የተከሰከሰዉ።በዘገባዉ መሠረት አዉሮፕላኑ መሬት እንደደረሰ ጋይቷል።በዚሕም ምክንያት አንዳድ ምንጮች እንደሚሉት አዉሮፕላኑ አሳፍሯቸዉ የነበሩ ሁለት መቶ ሰማንያ መንገደኞችና አሥራ-አምስት ሠራተኞቹ በሙሉ አልቀዋል።ምሥራቃዊ ዩክሬን የጦር ቀጠና በመሆኑ አዉሮፕላኑ ሳይመታ አይቀርም ብለዉ የሚጠረጥሩ አሉ።የዩክሬን መንግሥት አውሮፕላኑ አማፅያኑ በተኮሱት ሚሳይል ተመቶ ወድቋል ሲል አማፅያኑ ይህን በማስተባበል አውሮፕላኑ በዩክሬን መንግሥት ኃይሎች ተመቶ ነው የወደቀው ብለዋል ። ማሌዢያ ባለፈዉ መጋቢት 222 መንገደኞችንና 12 ሠራተኞቹን አሳፍሮ ሲበር ደብዛዉ በጠፋዉ አዉሮፕላኗ ከደረሰባት ድንጋጤና ሐዘን ገና አላገገመችም።