1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስፖርት ዝግጅት

ማክሰኞ፣ መጋቢት 17 2011

በዴንማርክ ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮን ውድድር 582 ታዋቂ አትሊቶች ከ 67 ሀገሮች ተሳታፊ እንደሚ ሆኑ የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፊዲሪሽን ትናንት አስታውቀዋል። በዚህ ውድድር  14 ኢትዮጵያውያን ወንድ እና 14 ሴት አትሊቶች በአዋቂና በ ከ20 አመት በታች በሚደረገው ውድድር ተሳታፊ እንደሚሆኑ የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፊዲሪሽን አስታውቋል። 

https://p.dw.com/p/3FeLZ
Fußball Länderspiel Niederlande - Deutschland | Serge Gnabry und Leroy Sane
ምስል picture-alliance/dpa/F. Gambarini

ትላንት በሚላን በተካሂደው የግማሽ ማራቶን ውድድር በ ሁለቱም ፆታ ኬንያውያን አትሌትች አሽናፊ ሆነዋል ።ሞቃታማ አየር በተካሄደው የትንንቱ ውድድር ኢትዮጵያዊትዋ አትሊት መሰረት መልካ አስቀድማ መሪነቱን ይዛ ነበር ፥ ከሁለት አመት የወሊድ እረፍት በኋላ ወደ ውድድር የተመለሰችው  ኬንያዊት አትሌት ፕሪስካ ጂፕቶ 1፡08፡26 በመግባት ቀዳሚ ስትሆን ፥መሰረት መልካ 1፡10፡39 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ሆናለች ሊላዋ ኪንያዊት አትሊት ሙርጊ ዋመቡኢ ሶስተኛ ሆናለች። በተመሳሳይ በተካሄደው  የወንዶች ውድድር  ኬንያውያን አትሊቶች ከ1 እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ አሽናፊ ሆነዋል። የፊታችን ቅዳሚ በዴንማርክ ለሚካሂደው የ ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮን ውድድር 582 ታዋቂ አትሊቶች ከ 67 ሀገሮች ተሳታፊ እንደሚ ሆኑ የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፊዲሪሽን ትናንት አስታውቀዋል። በዚህ ውድድር  14 ኢትዮጵያውያን ወንድ እና 14 ሴት አትሊቶች በአዋቂና በ ከ20 አመት በታች በሚደረገው ውድድር ተሳታፊ እንደሚሆኑ የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፊዲሪሽን ያወጣው ዝርዝር ያሳያል። በሁለቱም ፆታ በነጠላ አሽናፊው ቀዳሚ የሚሆኑ ት አትሊቶች 30•000  የአሚሪካ ዶላር ሽልማት ያገኛሉ። በዚህ ውድድር ከ 1 -6ኛ የሚወጡ አትሊቶች እያንዳንዳቸው የገንዘብ ሽልማት ሲኖራቸው ሽልማቱ የሚሰጠው አትሊቶች ከአበረታች ንጥረ ነገር ምርመራ ነፃ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ ነው።

EM Quali Montenegro - England
ምስል picture-alliance/SOLO Syndication/A. Hooper

የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ

ለ አፍሪካ ዋንጫ ፍልሚያ ያለፍት 24 ሀገሮች በሳምንቱ መጨረሻ በተደረጉት ጨዋታዎች ተለይተዋል። በመጭው ሰኔ እና ሀምሊ ወር ላይ ለሚካሂደው የዘ ንድሮ የአፍሪካ ሀገሮች  ዋንጫ ውድድር ለማለፍ በየምድባቸው የመጨረሿ የማጧሪያ ውድድር ትላንት እና ካትላንት በስቲያ ቅዳሚና አርብ በተለያዪ ሀገራት ተካሂደዋል በ ንጉስ ሉዊስ ርወጋሶር ስታድየም በተደረጋው በዚህ ጨዋታ ብሩንዲ በታሪክዋ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ሀለፊ ሆናለች።ግብፅ ለምታስተናግደው የዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ አቻ መውጣት ብቻ የሚጠበቅበት የብሩንዲ ብሔራዊ ቡድን ከትናንት በስቲያ ቅዳሚ ከጋቦን ብሔራዊ ቡድን ጋር ባደረገችው ጨዋታ 1ለ 1 በመለያየት ከምድብ ሥስት አስቀድማ ማለፍዋን ያረጋገጠችውን ማሊን ተከትላ ሁለተኛ በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪቃ ዋንጫ ጨዋታ ሃላፊ ሆናለች።

ሀና ደምሴ

ኂሩት መለሰ