1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመድኃኒት ጥራት ጥያቄ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 8 2009

በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ሰዎች ሲታመሙ መድኃኒት መዉሰዳቸዉ እንግዳ ነገር አይሆንም። የሚወስዱት መድኃኒት  ህመማቸዉን ማስታገስ ብሎም ማስወገድ ሲሳነዉ ግን፤ የወሰዱትን መድኃኒት ተብዩ ምንነት እንዲጠራጠሩ፤ ብሎም እንዲጠይቁ ግድ ይላቸዋል። አንድ አድማጫችን ኦሪጅናል መድኃኒቶችን እንዴት መለየት ይቻላል ሲሉ ጠይቀዉናል።

https://p.dw.com/p/2d4X8
Symbolbild Aids Medikament
ምስል picture-alliance/dpa/J. Kalaene

የመድኃኒት ጥራት ጥያቄ

የዲላዉ ነዋሪ ጠያቂያችን ጥያቄያቸዉን በላኩበት በደብዳቤ እንደዘረዘሩልን፤ በተለያዩ ጊዜያት የገዟቸዉመድኃኒቶች የተጻፉበት የፊደል ዓይነት እና መጠን የተለያየ ነዉ፤ አንደኛዉ በትልቅ ሌላኛዉ በትንንሽ። ስማቸዉ አንድ ሆኖ ሳለ ያስከተሉት ዉጤት ግን ተለያይቶ እሳቸዉ በህመም ሊሰቃዩ ግድ ሆኖባቸዋል። የአንድ መድኃኒትን ትክክለኛነት እንዴት መለየት ይችላል? አቶ ዘላለም ዘሪሁን ፋርማሲስትነት ናቸዉ፤ እዚህ ጀርመን ሀገር በሙያቸዉ ያገለግላሉ።  ስለመድኃኒቶች የፈዉስ አቅም እና የጥራት ልዩነት ከባለሙያ ማብራሪያ እንድናፈላልግ ከአንድ አድማጫችን ለቀረበልን ጥያቄ ጊዚያቸዉን ወስደዉ በዛሬዉ ዝግጅታችን ሙያዊ ማብራሪያቸዉን ሊሰጡን ፈቃደኛ ሆነዋል። አቶ ዘላለምን በቅድሚያ እስከ ኦሪጅናል ስለሚባሉትና ስላልሆኑት መድኃኒቶች አብራሩልን ብለናቸዋል።ከኢትዮትዮጵያም መድኃኒት ወደ ሀገር ስለሚገባበትና ገበያዉ ላይ ስለሚገኙ መድኃኒቶችም የሚመለከታቸዉን ለማነጋገር ጥረት ጀምረናል። ጤናችንን ለማግኘት ብለን የምንወስዳቸዉ መድኃኒቶች ጉዳይ ትኩረት ያሻዋልና።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ