1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመድኃኒት ቁጥጥርና ክትትል በኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ ጥር 3 2008

የኢትዮጵያ የምግብ የመድኃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለስልጣን ወደሀገር ዉስጥ በሕጋዊ መንገድ የሚገቡትንም ሆነ እዚያዉ የሚመረቱትን መድኃኒቶች የጥራት ደረጃ ይከታተላል።

https://p.dw.com/p/1Hc5y
Symbolbild Medikamente Pillen
ምስል Colourbox

የመድኃኒት ቁጥጥርና ክትትል በኢትዮጵያ

ከሳምንታት በፊት ወደሀገር ዉስጥ መድኃኒቶች በሕገወጥ መንገድ ገብተዉ መያዛቸዉ ተሰምቷል። መድኃኒቶች እንዲህ ባለ መንገድ መግባታቸዉ አዲስ ክስተት ባይሆንም፤ ሕገወጥ የሚባሉት መድኃኒቶች በተጠቃሚዉ ጤና ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉት ችግር ይኖር ይሆን መባሉ ግን አይቀርም። ኢትዮጵዉያን እንዳይጠቀሙት የተባለ የህመም ማስታገሻ ጉዳይም አለ። የመድኃኒት ጥራት እና ቁጥጥር በየሀገሩ ማድረግ የተለመደ ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ አሠራሩ ምን ይመስላል? መድኃኒቶችንም ሆነ ምግቦችን በተመለከተ ለሚያጋጥሙ ችግሮች ተገቢዉ ጥንቃቄ እንዲደረግ መጠቆም የሚችሉበትን አድራሻ ያዉቃሉ? ከባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ዝርዝር ማብራሪያ አግኝተናል። ከድምጽ ዘገባዉ ይከታተሉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ