የመድሃኒት አወሳሰድ ጥንቃቄ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 30 2004ማስታወቂያ
ባክቴሪዎች ፀራቸዉን ይለምዱትና በመድሃኒቱ መፈወስ ያቅታል። የዕለቱ ጤናና አካባቢ መሰናዶ ባለሙያ በማነጋገር ትኩረቱን እዚህ ላይ አድርጓል። መድሃኒት ስለሚላመድ የበሽታ ሁኔታ በተደጋጋሚ ይነገራል። እዚህ ጀርመን ቤርጊሽግላድባህ በተሰኘች ከተማ ማሪየን ሆስፒታል የሚሰሩት የአጥንትና ጠቅላላ ህክምና ባለሙያ ዶክተር ንጉሤ በቀለ በተለይ አንቲባዮቲክ በመባል ስለሚታወቁ መድሃኒቶች አወሳሰድና ሊደረግ ስለሚገባዉ ጥንቃቄ ማብራሪያ ሰጥተዉናል። ሃኪሞች መድሃኒትን ሲያዙ የተወሰነለትን የጊዜ ገደብ ጠብቆ አለመዉሰድ ሊያስከትል ስለሚችለዉ ችግርም ባለሙያዉ አብራርተዉልናል።
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ