1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ህብረት ጥረት

ሰኞ፣ ጥር 28 2010

የአውሮጳ ህብረት እና አባል ሀገራቱ የመካከለኛው ምሥራቅ ዪ,ሰላም ሂደቱ እንዲቀጥል የበኩላቸውን እየጣሩ ነው።

https://p.dw.com/p/2sALk
Mogherini Debatte im Europaparlament zur Anerkennung Palästinas 26.11.2014
ምስል picture-alliance/dpa/P. Seeger

የመካከለኛው ምሥራቅ የሰላም ሂደት እና የአውሮጳ ኅብረት

ባለፈው ታህሳስ መጀመሪያ ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለእየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማነት እውቅና ከሰጡ ወዲህ የመካከለኛው ምሥራቅ የሰላም ሂደት ውሉ የጠፋ ይመስላል። የትራምፕ እርምጃ የሰላም ድርድሩን ውጤት በተስፋ ሲጠባበቁ የነበሩ ፍልስጤማውያንን አሳዝኗል። የአውሮጳ ህብረት እና አባል ሀገራቱ የሰላም ሂደቱ እንዲቀጥል የበኩላቸውን እየጣሩ ነው። የዛሬው ማህደረ ዜና የመካከለኛው ምሥራቅ የሰላም ሂደት የገባበትን አጣብቂኝ እና የአውሮጳ ህብረትን ጥረት ይቃኛል።

ገበያው ንጉሴ 

ኂሩትመለሰ