1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመኢአድ ጋዜጣዊ መግለጫ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 24 2008

የድርጅቱ ባለሥልጣናት በንባብ ባሰሙት ባለ-ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ ያቀረቧቸዉ ጥያቄዎች ባስቸኳይ ካልተሟሉ ፓርቲያቸዉ ከሕዝብ ጎን ቆሞ በሰላማዊ መንገድ እንደሚታገል አስጠንቅቀዋል።

https://p.dw.com/p/1JsEQ

[No title]

የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ትናንት በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች ለተቃዉሞ አደበባባይ በወጡ ሠላማዊ ሰልፈኞች ላይ የወሰዱትን የሐይል እርምጃ የግፍ ጭፍጨፋ በማለት አወገዘዉ።የኢትዮጵያ መንግሥት ሕገ-ወጥ በሚል ሽፋን የሠላማዊ ዜጎችን ቤት እያፈረሰ ነዋሪዎችን ማፈናቀሉን እንዲያቆምም ድርጅቱ ጠይቋል።የድርጅቱ ባለሥልጣናት በንባብ ባሰሙት ባለ-ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ ያቀረቧቸዉ ጥያቄዎች ባስቸኳይ ካልተሟሉ ፓርቲያቸዉ ከሕዝብ ጎን ቆሞ በሰላማዊ መንገድ እንደሚታገል አስጠንቅቀዋል።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ