1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃውሞ በቻድ

ቅዳሜ፣ ጥር 26 2010

በቀጣናው በሚደረገው የጸረ-ሽብር ዘመቻ እና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት በሚደረጉ ጥረቶች ቁልፍ ሚና እንዳላቸው የሚነገርላቸው ፕሬዝዳንት ኤድሪስ ዴቤ በቻድ ዜጎች ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት እምብዛም ነው። ባለፈው ወር እንኳ በአገሪቱ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ ከ100 በላይ ሰዎች በፖሊስ ታስረው ነበር።

https://p.dw.com/p/2s5RR
Präsident Tschad - Idriss Déby Itno
ምስል UImago/Xinhua/C. Yichen

ተቃውሞ በቻድ

ቻድን ለ28 አመታት አንቀጥቅጠው የገዙት ፕሬዝዳንት ኤድሪስ ዴቤ ከአገራቸው ዜጎች ይልቅ በውጭ አገራት መሪዎች ዘንድ የተሻለ ተቀባይነት እንዳላቸው ይነገራል። አገሪቱ በቅጡ የሰለጠነ ወታደራዊ ኃይልም አላት። ፕሬዝዳንቱ በጥብቅ ይቆጣጠሩታል የሚባለው ጦር ናይጄሪያ፣ ኒጀር እና ካሜሩንን በመሳሰሉ አገሮች ለተልዕኮ ሲሰማራ ይታያል። በቀጣናው በሚደረገው የጸረ-ሽብር ዘመቻ እና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት በሚደረጉ ጥረቶች ቁልፍ ሚና እንዳላቸው የሚነገርላቸው ዴቤ ታዲያ በቻድ ዜጎች ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት እምብዛም ነው። ባለፈው ወር እንኳ በአገሪቱ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ ከ100 በላይ ሰዎች በፖሊስ ታስረው ነበር። በዛሬው የትኩረት በአፍሪቃ መሰናዶ በቻድ የፕሬዝዳንት ኤድሪስ ዴቤ አስተዳደር ላይ በሚሰነዘረው ተቃውሞ ዙሪያ ያጠነጥናል።

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ 

ይልማ ኃይለሚካኤል 

እሸቴ በቀለ