የመንግሥት ማሳሰቢያ
ሰኞ፣ ግንቦት 12 2011ማስታወቂያ
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ጥያቄዎቻችን ይመለሱ በሚል ትምህርት አድማ ላይ የነበሩ የተወሰኑ የዩኒቨርሲቲ እጩ ሐኪሞች አሁንም ወደ ትምህርታቸው አለመመለሳቸውን ገልጿል። የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ከእጩ ሐኪሞቹ ጋር በተደረገ ውይይት አብዛኞቹ ወደ ትምህርታቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል። ወደ ትምህርት ገበታቸው ያልተመለሱት በዚሁ አቋማቸው የሚጸኑ ከሆነ ከግማሽ የትምህርት አመት እስከ አንድ አመት ድረስ ከትምህርታቸው የመታገድ ከፍ ካለም እስከ መጨረሻው የመባረር ቅጣት ሊጠብቃቸው ይችላልም ሲሉ አሳስበዋል። ቅጣቱ ተግባራዊ የሚሆነውም የየዩኒቨርሲቲዎቹ ሴኔት በሚያሳልፈው ውሳኔ መሠረት መሆኑን ሚኒስትር ዴታው ተናግረዋል። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል፤
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ