የመብት ጥሰት እና መኢአድ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 19 2007ማስታወቂያ
የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በተለያዩ አካባቢዎች በሚኖሩ ዜጎች ላይ ይፈፀማል ያለዉን በደል የኢትዮጵያ መንግሥት ባስቸኳይ እንዲያስቆም ጠየቀ።ተቃዋሚዉ ፓርቲ ባወጣዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ በዜጎች ላይ የሚደርሰዉን መፈናቀል፤እስራት እና ግድያ መንግሥት ካላስቆመ ፓርቲዉ ሠላማዊ ትግል በሚጠይቀዉ አማራጭ በሙሉ መንግሥትን ይታገላል።የኢትዮጵያ የፌደራል ጉዳዮች ሚንስቴር በተለይ ጋምቤላ አካባቢ ተቀስቅሶ የነበረዉ ግጭት በመንግሥት ጥረት መቆሙን አስታዉቋል።
ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ