1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመስቀል በዓል አከባብር-በጀርመን

ሐሙስ፣ መስከረም 24 2005

በኢትዮጳያ ዉሃን ጠጥቶ፤ እሸትዋን በልቶ፤ ያደገ ዜጋ ሁሉ፤ ምን ከአገር ርቆ ቢሄድ፤ ያደገበትን ባህሉን ይረሳል ማለት ዘበት ነዉ። በዉጭ አገር ሲኖር፤ ዘመን መለወጫ እንዲሁም የተለያዩ የመንፈሳዊ በዓላት፤ በኢትዮጳያ በሚከበርበት ቀንም ባይሆን፤ እንደ አመችነቱ ታይቶ፤ በአዲሱ አገር ያፈራዉን ወዳጅ ጎረቤት ይዞ፤ ማክበሩ፤ አይቀሪ ነዉ።

https://p.dw.com/p/16JN8
ምስል DW

በኢትዮጳያ ዉሃን ጠጥቶ፤ እሸትዋን በልቶ፤ ያደገ ዜጋ ሁሉ፤ ምን ከአገር ርቆ ቢሄድ፤ ያደገበትን ባህሉን ይረሳል ማለት ዘበት ነዉ። በዉጭ አገር ሲኖር፤ ዘመን መለወጫ እንዲሁም የተለያዩ የመንፈሳዊ በዓላት፤ በኢትዮጳያ በሚከበርበት ቀንም ባይሆን፤ እንደ አመችዉ ተደርጎ በሚቀጥሉት ቀናት ወይም ሳምንታት ስራ እና ልጆች ትምህርት በሌላቸዉ ቀን፤ ኢትዮጳያዊዉ ማህበረሰብ፤ በአዲሱ አገር ያፈራዉን ወዳጅ ጎረቤት ይዞ፤ በአሉን በደማቅ ማክበሩ፤ ባህሉም አልባሳትን በማድረግ፤ እና ባንዲራዉን ከፍ አድርጎ በማዉለብለብ ማዉሳቱ ፤ማክበሩ፤ አይቀሪ ነዉ። ባለፈዉ ሰምወን  በኢትዮጳያ የተከበረዉ የመስቀል በዓል እዚህ በጀርመን በሳምንቱ መጨረሻ በደማቅ ስነ-ስርአት ተከብሮአል። በኮለኝ እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጳያዉያን በፍርንክፈርት ከተማ ከሚኖሩ ምዕመናን ጋር በጋራ የደመራን በዓል አክብረዋል። በበርሊን እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጳያዉያንም እንዲሁ በበርሊን ከተማ አክብረዋል። በአገራችን የመስቀል በዓል በሚከበርበት ወቅት፤ እዚህ በጀርመን የበጋዉ ወራት ተጠናቆ የመኸር ወቅት የሚጀምርበት በመሆኑ፤ ለችቦ የሚሆን ደረቅ ጭራሮ ፤ለደመራዉንም ቢሆን፤ ረጃጅም የዛፍ ግንዳሽ፤ የሚገኝበት በመሆኑ፤ ደመራዉን ለመደመር ቢበዛ ከግማሽ ቀን የበለጠ ስራ አይሆንም፤ ብቻ እሳት ለማንደድ ማለት ደመራዉን ለመለኮስ ከመዘጋጃ ቤት ፈቃድ መጠየቅ ስለሚያስፈልግ፤ በማመልከቻ የኢትዮጵያዊነት ባህላችንን ጠቅሶ፤ ፈቃድ የሚጠየቀዉ፤ የመስቀል በዓል ከመድረሱ ከሳምንታት በፊት ይሆናል። በጀርመን የደመራ በዓል እንዴት ተከበረ? ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!

Feier von Äthiopische orthodox Kirsche in Deutschland
ምስል DW

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ