1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመረጃ ፍሰትና ወጣቱ

ሰኞ፣ የካቲት 21 2003

በሰሜን አፍሪካና በአንዳንድ የአረብ ሀገራት የሚገኙ ወጣቶች የመብት ጥያቄን በማንገብ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ሲያከናውኑ ዋነኛ መሳሪያቸው አድርገው የተነሱት የመረጃ ፍሰትን ነው። እናስ ታዲያ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በሌሎች ሐገራት ስለሚገኙ ወጣቶች እንቅስቃሴ ምን ያህል ግንዛቤው አላቸው? መረጃዎችንስ በዋናነት ከየት ነው የሚያገኙት?

https://p.dw.com/p/R4Jf
የተቆለፈ ቤትና የመረጃ እጦት አንድ ናቸው
የተቆለፈ ቤትና የመረጃ እጦት አንድ ናቸውምስል Fotolia/Artsem Martysiuk
በሚል ከተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች የተውጣጡ ወጣቶችን አነጋግረናል። የወጣቶች መድረክ ክፍለ ግዜ ይቀጥላል። «በዓለማችን የመረጃ ፍሰትና ወጣቱ መረጃ የሚያገኝባቸው መንገዶች» ዋነኛ ርዕሳችን ነው። አሜሪካዊው ፀሀፌ-ተውኔት፣ ሃያሲና ባለቅኔ ቲ ኤስ ኤሊየት የመረጃ ወሳኝነትን አስመለከቶ ባንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር። «በመኖር ውስጥ ያጣነው ህይወት ከወዴት ይሆን የሚገኘው? በእውቀት ውስጥ የሳትነው ጥበብ እምን ውስጥ ነው ያለው? በመረጃ ውስጥ ያጣነውስ እውቀት የቱ ጋር ነው የሚገኘው?» መረጃ ለሰው ልጅ እጅግ ሲበዛ አስፈላጊ ነገር ነው። በቱኒዚያና በግብፅ የሚገኙ ወጣቶች ለዘመናት አንቀጥቅጠው እንደገዟቸው የሚነገርላቸውን መሪዎቻቸውን ያስወገዱት በዋነኛነት በመረጃ ድጋፍ ነው። ማንተጋፍቶት ስለሺ ሂሩት መለሰ