የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት«መኢአድ» ጥሪ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 21 2007ማስታወቂያ
የኢትዮጵያው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በምህፃሩ «መኢአድ»፣ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ዜጎች የሚፈናቀሉበትንና ንብረትም እንዲወድም የሚደረግበትን እርምጃ የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲያጣራ ጥሪ አቀረበ ። መኢአድ ዛሬ በአዲስ ፅህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ፣ መንግሥት በደሉን የፈፀሙትን ግለሰቦች ለፍርድ እንዲያቀርብና ለችግሩ ሰለባዎችም ድጋፍ እንዲሰጥ ጠይቋል ። የመብት ተሟጋቾችም ችግሩን ለዓለም ዓቀፉ ማህብረሰብ እንዲያሳውቁ መኢአድ ጥሪ አስተላልፏል ። ጋዜጣዊ መግለጫውን የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታትሎታል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ