1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕፃናት የጉልበት ብዝበዛ ይገታ

ዓርብ፣ ሰኔ 5 2001

የተመድ ዓለም ዓቀፍ የሰራተኛ ድርጅት ILO የፋይናንስ ቀዉሱ በአጠቃላይ ሕፃናትን፤ ከምንም በላይ ደግሞ፤ ታዳጊ ሴቶችን ለከፋ የጉልበት ብዝበዛ ሳይዳርግ እንደማይቀር ከወዲሁ አሳሰበ።

https://p.dw.com/p/I8HR
...በህንድ ታዳጊዋ በሥራ ላይ...ምስል AP

አዝማምያዉም የሕፃናትን የጉልበት ብዝበዛ ለመግታት ላለፉት አስርት ዓመታት የተደረገዉን ጥረት ሊያስተጓጉል እንደሚችል ድርጅቱ በህፃናት ላይ የሚፈፀመዉን የጉልበት ብዝበዛ የሚቃወምበት ዓለም ዓቀፍ ዕለት ታስቦ የሚዉልበትን የዛሬዉን ቀን አስመልክቶ ባወጣዉ መግለጫ አስታዉቋል። ለዘጠነኛ ጊዜ በዓለም ዙሪያ ታስቦ በሚዉለዉ በዚህ ዕለት ILO ለታዳጊ ሴቶች እድል ይሰጣቸዉ የሚል መፈክር አስተጋብቷል።

አዜብ ታደሰ/ሸዋዬ ለገሠ