1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕዝብ አስተያየት በህዝብ እና በቤቶች ቆጠራ

ዓርብ፣ የካቲት 8 2011

በተለይ 3ኛው የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ግልጽ ችግር እንደነበረበት እና መስተካከል እንዳለበት ታምኖ የቆጠራ ካርታው በጥንቃቄ ተሰርቷል ያለው ማእከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ሳይካለል የቀረ ቦታ አለመኖሩንና የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት ተሰርቷል ብሏል፡፡

https://p.dw.com/p/3DSZX
Blick aus meinem Fenster Addis Abeba Äthiopien
ምስል Solomon Mengist

4ተኛው የህዝብ እና የቤቶች ቆጠራ 

ኢትዮጵያ የምትከተለው ብሄር ተኮር የፖለቲካ ስርአት በቀደሙት የሕዝብ እና የቤቶች ቆጠራዎች ላይ ትልቅ አሉታዊ ጫና አሳርፎ እንደነበር አንድ ምሁር ለ«DW» ተናገሩ፡፡  ጉዳዩ ከህዝቦች ህልውና ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያለው በመሆኑ ዜጎች ከ 1 ወር በኋላ በሚደረገው ቆጠራ ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ምሁሩ ጠይቀዋል፡፡ ከመጋቢት 29፣2011 ጀምሮ ለሚካሄደው 4ኛው የኢትዮጵያ ቤቶች እና ህዝብ ቆጠራ 150 ሽህ የቆጠራ ቦታዎች መካለላቸውን፡ 190 ሽህ ሰዎችም በቆጠራው እንደሚሳተፉ እና ስራው ዲጂታል በሆነ ዘመናዊ መሳሪያ ታግዞ በልዩ ክትትል እንደሚከናወን የማእከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ለ DW አስታውቋል። ስራው በትክክል በተያዘለት ቀነ ገደብ ከተከናወነ ውጤቱ ነሐሴ ወር መጀመርያ አካባቢ እንደሚታውቅም ተገልጿል፡፡ 4ኛው የቤቶች እና ህዝብ ቆጠራ ከ 1 ዓመት በፊት ህዳር 2010 አ/ም መካሄድ የነበረበት ቢሆንም ሃገሪቱ ገጥሟት የነበረው ቀውስ እና አለመረጋጋት ቆጠራው በ 1 ዓመት እንዲራዘም ምክንያት ሆኗል፡፡ በተለይ 3ኛው የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ግልጽ ችግር እንደነበረበት እና መስተካከል እንዳለበት ታምኖ የቆጠራ ካርታው በጥንቃቄ ተሰርቷል ያለው ማእከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ሳይካለል የቀረ ቦታ አለመኖሩንና የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት ተሰርቷል ብሏል፡፡ ለ 4ኛው ህዝብና ቤቶች ቆጠራ 3.5 ቢሊዮን ብር መመደቡም ተገልጿል፡፡

ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ