1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕዋ ምርምና የቴሌስኮፕ ተከላ

ዓርብ፣ ጥቅምት 15 2006

ሁለት ታላላቅ አቅርበዉና አጉልተዉ የሚያሳዩ መነጽሮች ወይም ቴሌስኮፕ እንጦጦ ተራራ ላይ ትናንት መተከላቸዉ ተሰምቷል።

https://p.dw.com/p/1A6NP
ምስል DW/Getachew Tedla Hailegiorgis

ወደ15 ሺ ኪሎ እንደሚመዝኑ የተነገረዉ አቅርቢና አጉሊዉ መነጽሮቹ በሕዋ ብቻ ሳይሆን የመሬትን ምርምርም ሆነ የአየር ንብረት ጉዳይ ላይ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ እንዳለም ተገልጿል። በእንጦጦ በከፍተኛ ወጪ የተገነባ የህዋ ሳይንስ ቴክኒዎሎጂ የምርምርና ማሰልጠኛ ማዕከል ተጠናቆም ለሥራ ዝግጁ መሆኑን የቴሌስኮፖቹ ተከላ ሲከናወን በስፍራዉ የተገኘዉ ዘጋቢያችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ በዘገባዉ ጠቅሷል። በስራዉ የተሳተፉትን ባለሙያዎች በማነጋገር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ