1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሐረር የመጠጥ ዉሐ እጥረት

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 17 2002

የሐረር ከተማ ነዋሪዎች አንዱ እንዳሉት የዉሐ ፕሮጄክት ያልቃል-በሚለዉ በባለሥልጣናት ቃል-ብቻ ነዋሪዉን ሊያልቅ ነዉ።

https://p.dw.com/p/KGaj
ምስል Isabel Schlerkmann
የሐረር ከተማ የመጠጥ ዉሐ እጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን የከተማይቱ ነዋሪዎች አስታወቁ።ነዋሪዉ እንደሚለዉ የዉሐ እጥረቱን ለማቃለል የአካባቢ መስተዳድርና ማዕከላዊ መንግሥት በየጊዜዉ የሚነድፏቸዉ እቅዶችም ከተስፋ አላለፉም።የዉሐ ችግር የግንባታ፥ የሆቴልና የአገልግሎት መስጪያ ተቋማትን ሥራም እያወከዉ ነዉ።የድሬዳዋዉ ወኪላችን ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ካነጋገራቸዉ የሐረር ከተማ ነዋሪዎች አንዱ እንዳሉት የዉሐ ፕሮጄክት ያልቃል-በሚለዉ በባለሥልጣናት ቃል-ብቻ ነዋሪዉን ሊያልቅ ነዉ። ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር ነጋሽ መሐመድ