1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተሸለሙ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 13 2004
https://p.dw.com/p/13Yek
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተሸለሙ
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተሸለሙ

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር  በላይ ካሳ ሳሳካዋ አፍሪቃን አሶሲየሽን ከተባለ ድርጅት መሸለማቸው ታወቀ። ፕሬፌሰሩ ለሽልማት የበቁት ድርጅቱ ከሚንቀሳቀስባቸው የአፍሪቃ ሀገራት ተወዳድረው በተለይም የግብርና ልማት ሰራተኞችን አቅም በማጎልበት ላበረከቱት አስተዋፅኦ እንደሆነም ተጠቅሷል። በሽልማቱ የላቀ  ዘላቂ የአስተዳደር ሜዳይ እና የ100 ሺህ ብር ለማግኘት በቅተዋል ሲል የድሬዳዋው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር በዘገባው ገልጿል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ