1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሊቢያዉ የእርስበርስ ጦርነት

ቅዳሜ፣ የካቲት 26 2003

በሊቢያ ምስራቃዊ እና ምዕራባዊ ክፍል በሞአማር ጋዳፊ ደጋፊ ወታደሮችና በሕዝባዊው ዓማጺያን መካከል የሚካሄደው ውጊያ ተባብሶ እንደቀጠለ ነው። በዉግያዉ ሁለቱም ወገኖች በአገሪቷ የሚገኙ ቁልፍ ቦታዎችን በእጃቸዉ ለማስገባት በመጣር መሆኑ ተመልክቶአል።

https://p.dw.com/p/R6dH
ዉዝግብ በሊቢያምስል AP

ዛሪ ማለዳ በተካሄደዉ ዉግያ ብቻ ከሃምሳ ሰዎች በላይ ህይወታቸዉን አጥተዋል፣ ከሁለቱም ወገን በርካቶች ቆስለዋል። ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ በሕዝባዊው ዓማጺያን እጅ ቁጥጥር ስር የገባችዉ አል-ዛዉያ ከተማ ዛሪ ማለዳ በኮሎኔል ጋዳፊ ልጅ በካሚስ ብርጌድ የሚመራው የመንግሥት ጦር ከተማዋን በጁ ለማስገባት ያደረገዉ ጥረት አለመሳካቱን ተቃዋሚዎች መግለፃቸዉ ሲነገር ከቀትር በኳላ የኮነሪል ጋዳፊ ወታደሮች በድጋሚ ከተማዋን ማጥቃት መጀመራቸዉ ተጠቅሶአል። በጥቃቱ የሲቪል መኖርያ ቤቶች በመድፍ ጋይተዋል። በመካከለኛዉ ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪቃ በተነሳዉ ዉዝግብ ሰበብ የነዳጅ ዘይት ዋጋ እጅግ ማሳቀቡ የአለም መንግስትን እያሳሰበ መሆኑ ታዉቋል።

አዜብ ታደሰ
መስፍን መኮንን