የቤተ ክርስቲያን መፍረስ እና ውዝግቡ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 26 2009ማስታወቂያ
በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ለገጣፎ ይገኝ የነበረው የዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን አለአግባብ ፈረሰብን ሲሉ ቁጣቸውን እና ሀዘናቸውን ገልጸዋል። የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ፣ታቦቱን ጨምሮ ሌሎች የአምልኮተ እግዚአብሔር መገልገያ ቁሳቁሶች በማይገባ ቦታ እንደተጣሉ ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ቤተ ክርስቲያኑ የከተማውን ፕላን ግንዛቤ ውስጥ ሳይስገባ የተሰራ ነው ያለው የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳዳር በበኩሉ ሲፈርስ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑን ለዶቼቬለ ገልጿል። መስተዳድሩ ቦታው ለቤተ ክርስቲያን የሚመጥን አይደለም ሲልም አስታውቋል። ሁለቱን ወገኖች ያነጋገረው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ