1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የለንደኑ ቃጠሎ

ረቡዕ፣ ሰኔ 7 2009

የሕንፃዉ ነዋሪዎች ግን ካንድ ዓመት በፊት ሕንፃዉን ያደሰዉን ኩባንያ ይወቅሳሉ።ኩባንያዉ ባንፃሩ ወቀሳዉን ዉድቅ አድርጎታል።የለንደን የእሳት አደጋ መከላከያ ኮሚሽነር ዳኒይ ኮተን እንደሚሉት ግን የእሳቱን መንስኤ ለመናገር አሁን ጊዜዉ አይደለም

https://p.dw.com/p/2eiql
Großbritannien Großbrand in Londoner Hochaus
ምስል picture-alliance/Zumapress

ለንደን-ብሪታንያ ዉስጥ የሚገኘዉን ባለ 24 ፎቅ አፓርትመት ያጋየዉ እሳት መንስኤ የሕንፃዉን ነዋሪዎች፤ የገነባዉን ኩባንያ እና የአካባቢዉን ባለሥልጣናት እያወዘጋበ ነዉ።ትናንት ለዛሬ አጥቢያ የተቀጣጠለዉ እሳት እስካሁን 12 ሰዉ ገድሎ፤ ሌሎች ሰባ-አራት ማቃጠሉ ተረጋግጧል።የሆስፒታል ምንጮት እንዳስታወቁት ከቁስለኞቹ ሃያዉ ክፉኛ በመጎዳታቸዉ ምናልባት ተጨማሪ ሰዉ ይሞት ይሆናል።እሳቱ የተቀጣጠለበት ምክንያት እስካሁን በዉል አልታወቀም።የሕንፃዉ ነዋሪዎች ግን ካንድ ዓመት በፊት ሕንፃዉን ያደሰዉን ኩባንያ ይወቅሳሉ።ኩባንያዉ ባንፃሩ ወቀሳዉን ዉድቅ አድርጎታል።የለንደን የእሳት አደጋ መከላከያ ኮሚሽነር ዳኒይ ኮተን እንደሚሉት ግን የእሳቱን መንስኤ ለመናገር አሁን ጊዜዉ አይደለም።«ምን እንደሆነ ለማወቅ ከተባባሪዎቻችን ጋር ሆነን እየሰራን ነዉ።የዚሕን እሳት መነሻ ለማወቅ እና ለመርመር በሚቀጥሉት ሰዓታት እና ቀናት በቅርብ መሥራታችንን እንቀጥላለን።በከተማ ዉስጥ የሚከሰቱ አደጋዎችን ሥለምንከላከልበት ሥልት ከሚያማክሩኝ ጋር የሚሠሩ የሥነ-ሕንፃ ባለሙያ አግኝተናል።ሁለቱ በመተባበር ሕንፃዉ ፀንቶ የቆመ መሆኑን ያሳዉቁናል።ለጊዜዉ የእሳት መከላከያ ባለሙያዎችን ሥራ የሚያዉክ ነገር  ሕንፃዉ ዉስጥ የለም።» 
ግሪን ፌል የተሰኘዉ ባለ 24 ፎቅ ግዙፍ ሕንፃ የተሠራዉ እንደ ጎርጎሪያዉኑ አቆጣጠር በ1974 ነዉ።ባለፈዉ ዓመት በ11 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እድሳት ተደርጎለት ነበር።ዛሬ ጋየ። 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ