1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩኒሴፍ ዘገባ

ማክሰኞ፣ የካቲት 21 2009

የተመ የህፃናት መርጃ ድርጅት፣ «ዩኒሴፍ» በሰ/አፍሪቃ በኩል አድርገው ወደ አውሮጳ ለመግባት የሚሞክሩ ህፃናት ትልቅ አደጋ እንደተደቀነባቸው እና ብዙ እንግልትም እንደሚያጋጥማቸው አስጠነቀቀ። «ዩኒሴፍ» ይህን ይፋ ያደረገው «አደገኛው የህፃናት ጉዞ በማዕከላዊ የሜድትሬንያን ባህር፣የስደተኞች መስመር» በሚል ርዕስ ስር ዛሬ ባወጣው ዘገባው ነው።

https://p.dw.com/p/2YO3R
Das Logo und der Schriftzug der Hilfsorganisation UNICEF sind am 5. Februar 2008 an der Zentrale in Koeln zu sehen.
ምስል AP

Ber. Brüssel(UNICEF warnt vor Gefahren für Flüchtlingskinder in Nordafrika) - MP3-Stereo

በተለይ፣ ህፃናት እና ሴቶች ለወሲባዊ ጥቃት፣ ለብዝበዛ፣ እንዲሁም፣ ለሰው አሸጋጋሪዎች እና ለሊቢያ የፀጥታ ኃይላት የቁም ስቅል መከራ መጋለጣቸውን የ« ዩኒሴፍ»አስታውቋል።  እንደ ዘገባው፣ ባለፈው ዓመት ብቻ በዚሁ መስመር ከተጓዙት መካከል 4,579 ሰዎች ሰምጠው ሲሞቱ፣ ከነዚሁ መካከል ወደ 700 የሚጠጉት ህፃናት ነበሩ። የአውሮጳ ህብረት እነዚህን ለስቃይ እና መከራ የተጋለጡትህ ስደተኞች እንዲከላከል «ዩኒሴፍ» በዘገባው ጥሪ አቅርቧል። 

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ