1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሄልሙት ሽሚድት ሕልፈትና የሐዘን መግለጫዎች

ረቡዕ፣ ኅዳር 1 2008

የቀድሞዉ የጀርመን መራሔ መንግሥት ሄልሙት ሽሚድት ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ተከትሎ በርካታ የዓለም መንግሥታትና የመንግሥታት ተጠሪዎች ለጀርመን የኃዘን መግለጫዎቻቸዉን እያስተላለፉ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1H48k
Deutschland Kerzen und Blumen für Helmut Schmidt in Hamburg
ምስል Reuters/F. Bimmer

[No title]


የጀርመን በተለይ የሃንቡርግ ከተማ ነዋሪዎች የ 96 ዓመቱ ሄልሙት ሽሚድት መኖርያ ቤት አጠገብ በመሄድ ሻማ በማብራትና አበባ በማስቀመጥ ኃዘናቸዉን በመግለፅ ላይ ይገኛሉ። በጀርመን ሕዝብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበሩት ሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ አባልና የፖለቲካ ጉዳይ ተንታኝ ሄልሙት ሽሚዲት ባደረባቸዉ ሕመም ምክንያት፤ በመኖርያ ቤታቸዉ በሕክምና ሲረዱ ቆይተዉ ነዉ ትናንት ከቀትር በኋላ ሕይወታቸዉ ማለፉ የተነገረዉ ። የጀርመን ፖለቲከኞች የሄልሙት ሽሚትድን ከዚህ ዓለም በሞት መለየት በተመለከተ የሰጡትን አስተያየቶች የተካተካተበትን ዘገባ የበርሊኑ ወኪላችን አሰናድቶ ልኮልናል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ

አeያም ተክሌ