1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሃኖፈሩ የኢንዱስትሪ ትርዒት፣ ሥነ-ቴክኒክና ታዳሽ የኃይል ምንጭ፣

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 14 2001

በሰሜን ጀርመን በምትገኘው ፌደራል ክፍላተ-ሀገር ኒደርዛኽሰን (ታኅታይ ሳክሰኒ)ርእሰ ከተማ ሀኖፈር፣ ከ 61 አገሮች የተውጣጡ 6,100 ትርዒት አቅራቢዎች የሚሳተፉበት ፣

https://p.dw.com/p/Hc8R
አማራጭ፣ ታዳሽ የኃይል ምንጭን አመላካች፣ አረንጓዴ «ሶኬት»፣ በሃኖፈሩ ትርዒት፣
አማራጭ፣ ታዳሽ የኃይል ምንጭን አመላካች፣ አረንጓዴ «ሶኬት»፣ በሃኖፈሩ ትርዒት፣ምስል Deutsche Messe AG

የሥነ-ቴክኒክ ትርዒት ፣ ባለፈው ሰኞ የተከፈተ ሲሆን እስከፊታችን ዓርብ ለተመልካቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል። ትርዒቱን ባለፈው ሰኞ፣ መራኂተ-መንግሥት ወ/ሮ አንጌል ሜርክል 2 ሰዓት ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

«በቀውስ ውስጥ እየኖርን እንዲሁ አንመለከትም። የኢንዱስትሪ ኩባንያዎች ተጠናክረው ችግሩን እንዲወጡት እንፈልጋለን። በዚህ በሃኖፈሩ ትርዒት የዚህን የማገገም ምልክት ዐይቼአለሁ። መለስተኛ የኢንዱስትሪ ኩባንያዎች ትንንሸቹም ሆኑ ትልልቆቹ፣ ከባዱን የኤኮኖሚ ችግር ተቋቁመውና የደቀነውን ቅድመ-ግዴታ አሟልተው አዳዲስ የፈጠራ ውጤቶቻቸውን ይዘው ቀርበዋል። »

በዘንድሮው የሃኖፈር የኢንዱስትሪ ትርዒት ልዩ እንግዳ በመሆን ትርዒቷን በማቅረብ ላይ የምትገኘው ሀገር በሳይንስና ሥነ-ቴክኒክ ፣ በኤኮኖሚም እመርታ ያሳየችው ደቡብ ኮሪያ ናት።

ተክሌ የኋላ፣

አርያም ተክሌ፣