1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሁለቱ የሱዳን መንግሥታት ውዝግብ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 21 2004

የተመድ እና የአፍሪቃ ህብረት ሱዳንና ደቡብ ሱዳን በመካከላቸው ለቀጠለው ልዩነት መፍትሄ እንዲያስገኙ ያስቀመጡት የመጨረሻ የቀን ቀጠሮ የፊታችን ሀሙስ እአአ ነሀሴ ሁለት ያልፋል። ሁለቱን ሀገሮች የሚያወዛግቡዋቸው ብዙ ጉዳዮች ናቸው።

https://p.dw.com/p/15g1e
ዓለም አቀፍ የሱዳን ጉባዔ ቦንምስል Getty Images/AFP

የተመድ እና የአፍሪቃ ህብረት ሱዳንና ደቡብ ሱዳን በመካከላቸው ለቀጠለው ልዩነት መፍትሄ እንዲያስገኙ ያስቀመጡት የመጨረሻ የቀን ቀጠሮ የፊታችን ሀሙስ እአአ ነሀሴ ሁለት ያልፋል። ሁለቱን ሀገሮች የሚያወዛግቡዋቸው ብዙ ጉዳዮች ናቸው። የነዳጅ ዘይቱ ሀብት ገቢ ክፍፍል፡ ድንበራቸውን በትክክል መለየት እና የፀጥታ ጥያቄዎች ጥቂቶቹ ናቸው። ሰሞኑን በቦን ከተማ በተደረገውና በያመቱ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የሱዳን ጉባዔ የተካፈሉ ምሁራን፡ ተመራማሪዎችና የልማት ሰራተኞች በሁለቱ የሱዳን መንግሥታት መካከል እስከዛሬ እልባት ባልተገኘባቸው ጉዳዮች ላይ በሰፊው መክረዋል።

Karte Sudan mit Khartum und Abyei

ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን የተመድ እና የአፍሪቃ ህብረት ያስቀመጡት የቀነ ቀጠሮ ሳያልፍ በፊት ስምምነት የሚደርሱበት አጋጣሚ ከፍተኛ መሆኑን በቦን አለማቀፍ የሱዳን ጉባኤ ላይ የተሳተፉት ጉባይተኞቹ በጠቅላላ ይስማማሉ። ግን ስምምቱ ምን ያህል ዘላቂ እና አሳሪ በመሆኑ ጥያቄ ላይ፤ ጉባይተኞቹ ጥርጣሪ አላቸዉ። በሱዳን እና በአካባቢዉ ሃገሮች፤ ለብዙ አመታት የሰሩት እና ስለ ሱዳን በርካታ መጻህፍት ያወጡት፤ ዳግላስ ጆንሰን ሱዳን ከአሁን ቀደም ዲፕሎማቲካዊ ግፊት ሲደረግባት የደረሰቻቸዉ ስምምነቶች ያስገኙትን ዉጤት እንዲህ ገምግመዋል

«ዲፕሎማሲያዊ ግፊት በወረቀት የሰፈረ ስምምነት ሊባል የሚችል ዉል ሊያስገኝ ይችላል። ስምምነቱ በተግባር የሚተረጎምበት ሁኔታ ግን ቆይቶ ነዉ የሚወሰነዉ። በሌላ አነጋገር ስምምነት ተደርሶአል ሊባል አይችልም። እና በወቅቱ በሱዳን የሚታየዉን ሁኔታ እንዲሁም በሁለቱ የሱዳን መንግስታት መካከል የቀጠለዉን ዉዝግብ ስመለከት ለልዩነታቸዉ መፍትሄ እንዲያስገኙ የተቀመጠዉ የመጨረሻ የቀነ ቀጠሮ ሁለቱን አገሮች መወዛገብ ለቀጠሉት አሳሳቢ ጉዳዮች ስምምነት ያስገኛል ብዪ አላስብም።»

Konflik Sudan Südsudan
በሱዳን የግጭት ቦታምስል picture-alliance/dpa

ደቡብ ሱዳን ከአንድ አመት በፊት እ,አ,አ ሐምሌ 9 ቀን በይፋ ነፃ ሃገር ከመሆንዋ በፊት ነበር ድርድሩ የተጀመረዉ። ይሁንና የነዳጅ ዘይቱ ሃብት ክፍፍልን በተመለከተ ሱዳን በሃገርዋ በተዘረጉት የነዳጅ ዘይት ቧንቧዎች ለሚያልፈዉ የደቡብ ሱዳን ነዳጅ ዘይት፤ ከነፃነቱ በኋላ የጠየቀችዉ ከፍተኛ ክፍያ፤ ሁለቱን ሃገሮች ትልቅ ዉዝግብ ዉስጥ አስገብቶ፤ የነዳጅ ዘይት አቅርቦት ካለፉት በርካታ ወራት ወዲህ ለተቋረጠበት ድርጊት ምክንያት ሆንዋል። ይህም በሁለቱ አገሮች ኤኮነሚ ላይ፤ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶአል። በተለይ በሱዳን፤ የደቡብ ሱዳን ነዳጅ ዘይት አቅርቦት መቋረጡ፤ ያስከተለዉ የኑሮ ዉድነት፤ በሃገሪቱ ከአለፉት ወራት ወዲህ የህዝብ ተቋም ቀስቅሶአል። ሁኔታዎች ይህን በመሰሉበት በአሁኑ ግዜ፤ ደቡብ ሱዳን ባለፈዉ ሳምነት፤ በሱዳን ለሚያልፈዉ የነዳጅ ዘይትዋ፤ ከፍተኛ ዋጋ ለመክፈል እና፤ ሁለቱም አገሮች የባለቤትነት ይገባኛል ጥያቄ ባነሱበት፤ በነዳጅ ዘይት በታደለዉ በድንበሩ አካባቢ በሚገኘዉ አሁንም ሁለቱን ሃገሮች በሚያወዛግባዉ፤ የአብዪ ግዛት ዉስጥ፤ ህዝበ ዉሳኔ እንዲካሄድ ሃሳብ አቅርባለች። እስከ ትናንት ድረስ ሃሳቡን ዉድቅ አድርጋ የቆየችዉ ሱዳን፤ ለነዳጅ ዘይቱ የቀረበዉን የክፍያ ሃሳብ ልትደግፈዉ እንደምትችል በትናንቱ እለት ጠቁማለች። በሁለቱ አገሮች መካከል የነዳጅ ዘይት አቅርቦት ይከናወን ዘንድ ግን፤ አንዳንድ ሁኔታዎች ሊስተካክሉ እንደሚገባ በጀርመን የሱዳን አንባሳደር ሃሊድ ሙስጠፋ ዳፋል ገልጸዋል።

« የደቡብ ሱዳን ነዳጅ ዘይት በሱዳን ያልፍ ዘንድ ለጸጥታ ጉዳዮች መፍትሄ ማግኘት ግድ ነዉ። ደቡብ ሱዳን፤ በሱዳን መንግስት አንጻር የሚዋጉ አማያንን ማስታጠቅዋን በቀጠለችበት እና የጸጥታዉ ጥያቄ መልስ ባላገኝበት በአሁኑ ግዜ በነዳጅ ዘይት አቅርቦት ክፍያ ላይ የቀረበዉን የትብብር ሃሳብ በፍጹም ልንቀበል አንችልም»

ደቡብ ሱዳን ሁለቱን ሃገሮች በሚለየዉ ድንበር አካባቢ ባሉት የሱዳን የብሉናይ እና የደቡብ ኮርዶፋን ግዛቶች ዉስጥ በሱዳን መንግስት አንጻር የሚዋጉትን የአማጽያን ቡድኖችን ትረዳለች በሚል፤ ሱዳን ትወቅሳለች። እርግጥ በጁባ የሚገኘዉ የደቡብ ሱዳን መንግስት ይህንን ወቀሳ፤ በይፋ አስተባብሎአል። ግን በሁለቱ ግዛቶች የሚንቀሳቀሱት አማጽያን፤ አሁን በደቡብ ሱዳን መንግስቱን ያቋቋመዉ፤ የሱዳን ህዝብ ነጻ አዉጭ ንቅናቄ አባል እንደነበሩ ሲታወስ፤ ጁባ የተወሰነ እርዳታ ሳትሰጥ እንደማትቀር፤ ብዙዎች ይገምታሉ። ደቡብ ሱዳን በአወዛጋቢዉ የነዳጅ ዘይት ገቢ ክፍፍል ጉዳይ ላይ፤ ስምምነት ለመድረስ ስትል የቀድሞ ጓዶችዋን መርዳት ማቆምዋን፤ በቦኑ የሱዳን ጉባኤ የተካፈሉት ጠበብት ይጠራጠሩታል። የሁለቱ ሱዳን መንግስታት ፖለቲከኞች የሃሳብ ልዩነታቸዉን ማጥበብ ተስኖአቸዉ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት ግን፤ አሁን በድንበሩ አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦችን የሚረዳ ድርጅት ያቋቋሙት፤ የቀድሞዉ የደቡብ ሱዳን ም/ር ሉካ ቢዮን ዲንግ ኮንግ ገልጸዋል።

Südsudan Amum Sudan Hussein Verhandlungen Archivbild
ዓለም አቀፍ የሱዳን ጉባዔ ቦንምስል Getty Images/AFP

«አንዳንድ ሰሜን ሱዳናዉያን ከሰሜን ወደ ደቡብ እቃ በማመላለስ ህይወታቸዉን አደጋ ላይ ይጥላሉ። ከዝያ በተረፈ ግን በቦታዉ ሁኔታዎች የተረጋጉ ናቸዉ። ህዝቡ እለታዊ ኑሮዉን እየኖረ ነዉ።»

ዳንየል ፔልስ/አርያም ተክሌ

መስፍን መኮንን