1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓለም አቀፉ የጀግና ሴቶች ቀን 

ዓርብ፣ መጋቢት 22 2009

አቀፉ የጀግና ሴቶች ቀን ከ60 በላይ ሃገራት የመጡ ሴቶች በተገኙበት ረቡዕ መጋቢት 20 ቀን በዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒሥቴር መሥሪያ ቤት ተከብሯል። ሜላንያ ትራምፕ አምባገነን ስርዓትን፤ ጦርነትን ሙስናንና በሴቶች ላይ የሚፈፀመዉን አድሎ ተጋፍጠዋል የተባሉ 13 ሴቶችንም ተሸልመዋል።

https://p.dw.com/p/2aSRT
USA Washington 2015 International Women of Courage Award
ምስል picture alliance/AA/S. Corum

Ber.D.C (International Women Awards) - MP3-Stereo


ዓለም አቀፉ የጀግና ሴቶች ቀን ከ60 በላይ ሃገራት የመጡ ሴቶች በተገኙበት ረቡዕ መጋቢት 20 ቀን በዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒሥቴር መሥሪያ ቤት ተከብሯል። ከ 100 በላይ ሴቶች የተካፈሉበትን ይህን ዝግጅት በንግግር የከፈቱት አዲስዋ ቀዳማዊት እመቤት ሜሊንያ ትራምፕ ናቸዉ። ሜላንያ ትራምፕ አምባገነን ስርዓትን፤ ጦርነትን ሙስናንና በሴቶች ላይ የሚፈፀመዉን አድሎ ተጋፍጠዋል የተባሉ 13 ሴቶችንም ተሸልመዋል። አንድ የሴቶች ጉዳይ ተሟጋች ጉዳዩን አስመልክተዉ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ማብራርያ በአሉና ሽልማቱ አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል።

 
መክብብ ሸዋ 

አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ