1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውይይት፦ ፌዴራሊዝምና ዲሞክራሲያዊ ሽግግር በኢትዮጵያ

እሑድ፣ የካቲት 24 2011

የኢትዮጵያን የፌዴራል ሥርዓት አንዳንዶች በኢትዮጵያውያን መካከል መቃቃር እና ግጭት እንዲስፋፋ ያደረገ «የጎሣ ፌዴራሊዝም» ሲሉ ይኮንኑታል። ሌሎች በበኩላቸው፦ ኢትዮጵያውያን ቋንቋቸውን እና ባሕላቸውን እንዲያዳብሩ እድል ፈጥሯል በማለት ያወድሱታል። 

https://p.dw.com/p/3ELPc
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

ውይይት፦ «በፌዴራሊዝሙ አንደራደም አላልንም»

ኢትዮጵያ ኅዳር 29 ቀን፣ 1987 ዓ.ም በአዋጅ በጸደቀው ሕገ-መንግሥት መሰረት ካለፉት ኹለት ዐሥርተ-ዓመታት በላይ የምትመራው ቋንቋን መሰረት ባደረገ የፌዴራል ሥርዓት ነው። ይኽን ሥርዓት አንዳንዶች በኢትዮጵያውያን መካከል መቃቃር እና ግጭት እንዲስፋፋ ያደረገ «የጎሣ ፌዴራሊዝም» ሲሉ ይኮንኑታል። ሌሎች በበኩላቸው፦ ኢትዮጵያውያን ቋንቋቸውን እና ባሕላቸውን እንዲያዳብሩ እድል ፈጥሯል በማለት ያወድሱታል። 

ዲሞክራሲያዊ የለውጥ ሽግግር ላይ መኾኗ የሚነገርላት ኢትዮጵያ ፖለቲከኞቿ ሁሉን የሚያግባባ ኹነኛ የፖለቲካ ሥርዓት ለመመስረት ቁርጠኝነታቸውን ሲገልጡ ይደመጣል። መንግሥትም የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት ካላቸው ድርጅቶች ጋር ተቀራርቦ ለመሥራት ዝግጁ መኾኑን በተደጋጋሚ ይናገራል። 

በዚሁ ሳምንት እንደውም ገዢው ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶቹ ወደ አንድ ሀገራዊ ፓርቲ እንደሚቀየሩ ይፋ አድርጓል።  በሌላ በኩል የመንግሥት አካል የኾነው የኦሮሞ ዲሞክራሲ ፓርቲ በምኅጻሩ ኦዲፒ፦ «በፌዴራሊዝሙ አንደራደም» የሚል መግለጫ ሰጠ መባሉ መነጋገሪያ ኾኗል።  መግለጫው ኢትዮጵያ ጀምሬዋለሁ ባለችው ዲሞክራሲያዊ ሽግግር ሒደት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራል የሚል ስጋታቸውን የሚገልጡም ተበራክተዋል። «ፌዴራሊዝምና ዲሞክራሲያዊ ሽግግር በኢትዮጵያ» የውይይቱ ርእስ ነው።

ሙሉ ውይይቱን ለማድመጥ እታጥ ካለው የድምፅ ማጫወቻ ማግኘት ይቻላል። 
ማንተጋፍቶት ስለሺ