1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውይይት፦ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ ንግግርና አንድምታው

እሑድ፣ መጋቢት 30 2010

ባለፈው መጋቢት 24፣ 2010 ዓም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰየሙት ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ስልጣናቸውን በይፋ በተቀበሉበት ጊዜ ያሰሙት ንግግር ዛሬም ድረስ ብዙ እያወያየ ይገኛል።

https://p.dw.com/p/2vdB2
Äthiopien Vereidigung Premierminister Abiy Ahmed
ምስል picture-alliance/AA/M. W. Hailu

ውይይት፦ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ ንግግርና አንድምታው

ብዙዎች የዶክተር አቢይ ንግግርን በአዎንታዊ መንገድ እንደተመለከቱት ሁሉ ተግባራዊነቱን የተጠራጠሩትም ብዙዎች ናቸው። አንዳንዶች እንዲያውም አገሪቱን እየመራ ያለው አንድ ፓርቲ መሆኑን ያስረሳ የመሰለ ንግግር ነው ያሉት።የተቃዋሚ ቡድኖች እና የፖለቲካ ተንታኞች ጠቅላይ ሚንስትሩ ያነሷቸው ሀሳቦች ከልብ ከመለወጥ የተደረገ ንግግር መሆኑን  ጠብቀው ማየቱን መርጠዋል። ንግግሩ ራሱ በራሱ ፋይዳ አለው። አንዳንድ የተደመጡት ሀሳቦች ከተለመደው የኢህአዴግ አሰራር ወጣ ያሉ  ቢሆንም፣ የዚሁ ግንባር እና ገዢ ፓርቲ መሪ መሆናቸው መረሳት የለበትም፣ በዚህም የተነሳ  ኢትዮጵያ ለገጠማት ፈታኝ ሁኔታ እና ችግር ዘላቂ መፍትሔ ሆኖ ሊታይ እንደማይገባ ነው የተናገሩት። የዶክተር አቢያ አህመድ ንግግር እና አንደምታውን በተመለከተ ባካሄድነው ውይይት የተለያዩ አስተያየቶች ቀርበዋል።

አርያም ተክሌ

እሸቴ በቀለ