1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውይይት፦ የእስረኞች ፍቺ አንደምታ

እሑድ፣ ጥር 13 2010

የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ኢሕአዴግ በወሰነዉ መሠረት የሐገሪቱ መንግሥት የመሠረተባቸዉን ክስ አቋርጦ እንደሚለቅቃቸዉ ካስታወቀዉ 528 እስረኞች 115ቱ ባለፈዉ ረቡዕ መፈታታቸዉ ተዘግቧል። መንግሥት እስረኞቹን ለመልቀቅ የወሰነዉ «ለሐገራዊ መግባባት እና የዴሞክራሲ ምሕዳሩን ለማስፋት» መሆኑን አስታዉቋል።

https://p.dw.com/p/2rGLF
PK von Äthiopiens Generalstaatsanwalt
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

ውይይት፦ የእስረኞች ፍቺ አንደምታ

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ ባለፈው ሰኞ ጥር 7ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በቅርቡ ያካሄደውን ስብሰባ ሲያጠናቅቅ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት በእስር ላይ የሚገኙ 528 ተጠርጣሪዎች በይቅርታ ይፈታሉ ብለዋል፡፡ የመጀመሪያው ዙር የይቅርታ ሂደት እስከሚቀጥለው ሁለት ወራት እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት እርምጃ ከሁለት ዓመት በላይ ያስቆጠረዉን ሕዝባዊ ተቃዉሞ ለማቀዛቀዝ ወይም ምላሽ ለመስጠት ያለመ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ። የመንግሥት እርምጃ፤ ትክክለኛዉ ምክንያት እና ዉጤቱ የዚህ ሳምንት  ዉይይታችን ትኩረት ነዉ። ነጋሽ መሐመድ የመራውን ሙሉ ውይይት ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ነጋሽ መሐመድ