1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውይይት፦ አልረጋ ያለው የተሿሚዎች ወንበር

እሑድ፣ ሚያዝያ 20 2011

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እስካሁን ባካሄዷቸው ሹም ሽሮች አዳዲስ ተሿሚዎቻቸውን በብቃት፣ በልምድ እና በትምህርት ዝግጅታቸው እንደመዘኗቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል። ሆኖም ተሿሚዎቻቸው በአጭር ጊዜ ከቦታዎቻቸው ተነስተው ወይ ወደሌላ ተቋም ሲዘዋሩ አልያም ሲሻሩ ይስተዋላል። ይህ አካሄድ ጥያቄ በታዛቢዎች ዘንድ ጥያቄ ወልዷል።

https://p.dw.com/p/3HZAS
Äthiopien Addis Ababa - Äthiopiens neues Kabinett besteht zur Hälfte aus Frauen
ምስል Getty Images/AFP/Stringer

ውይይት፦ አልረጋ ያለው የተሿሚዎች ወንበር

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እስካሁን ባካሄዷቸው ሹም ሽሮች አዳዲስ ተሿሚዎቻቸውን በብቃት፣ በልምድ እና በትምህርት ዝግጅታቸው እንደመዘኗቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ እምነት እነዚህ ተሿሚዎች የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያነሳቸውን የሰላም፣ የልማት እና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች በብቃት የሚመልሱ ናቸው። በዚህ መልኩ መሾማቸው የተነገረ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ከጥቂት ቆይታ በኋላ በተደጋጋሚ ሲሻሩ ወይም ወደ ሌላ ተቋም ሲዛወሩም ታይቷል። 

የመንግስት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና ተቋማትን እንዲመሩ የተሾሙ ባለስልጣናት በየጊዜው ቶሎ ቶሎ መቀየያየራቸው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት የጠና አለመሆን ምልክት አድርገው የሚወስዱ አሉ። የመንግስት ተሿሚዎች እንዲህ በአጭር ጊዜያት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መዟዟራቸው እና መለዋወጣቸው መንግስት በሀገሪቱ ሊተገብረው በሚያስበው ለውጥ ወይም ማሻሻያ ላይ ተጽዕኖ እንደሚሳድርም ይነሳል። የ“እንወያይ” መሰናዷችን በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በሚስተዋሉ ሹም ሽሮች፣ መንስኤዎች እና መፍትሔው  ላይ ያተኩራል። 

 

ተስፋለም ወልደየስ 

ነጋሽ መሐመድ