1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሳዑዲ የምህረት አዋጅ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 27 2009

ኤምባሲው እንዳስቀመጠው የምህረት አዋጁን ተጠቅመው ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ቁጥር እጅግ ጥቂት ነው፡፡ የምህረት ጊዜውን ተጠቅመው ከሳዑዲ ለመውጣት ያልፈለጉ ዜጎች ጉዳይ እጅግ እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እየገለጸ ነው።

https://p.dw.com/p/2cTot
Saudi-Arabien Delegation aus Äthiopien
ምስል DW/S. Shebiru

MMT-Ber. Riyadh Ethiopians & the Saudi Amnesty - MP3-Stereo

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ሕገወጥ የሚላቸው የውጭ ዜጎች በፈቃደኝነት እንዲወጡ ያስቀመጠው የዘጠና ቀን የምህረት ጊዜ 35 ቀኖች አለፈው፡፡ ሕገወጥ በተባለው መንገድ በሳዑዲ ይኖራሉ ከሚባሉት በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን በኤምባሲው ጽሕፈት ቤቶች ቀርበው የጉዞ ሰነድ የወሰዱት ቁጥር ከአስር ሺህ በታች መሆኑን በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ይገልጻል፡፡ የምህረት አዋጁን ተጠቅመው ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ደግሞ ኤምባሲው እንዳስቀመጠው እጅግ ጥቂት ነው፡፡ የምህረት ጊዜውን ተጠቅመው ከሳዑዲ ለመውጣት ያልፈለጉ ዜጎች ጉዳይ እጅግ እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እየገለጸ ነው። የሪያዱ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ አለው።

ስለሺ ሽብሩ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ