1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውይይት፤ ሐሳብን የመግለጽ መብትና ፀረ-ሽብር ሕጉ

እሑድ፣ ጥቅምት 14 2008
https://p.dw.com/p/1Gtsn

ዞን ዘጠኝ በመባል የሚታወቁትና በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ቀርቦባቸው ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር በእስር ላይ የነበሩት ጋዜጠኞችና የድረ-ገጽ ፀሐፍት ክሱ ተነስቶላቸዋል። ድረ- ገፅ ተጠቅመው የተለያዩ ፅሁፎችን በማውጣት ሕገ- መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ከተከሰሱት የድረ-ገፅ ፀሐፍት መካከል አምስቱ ታሳሪዎች ባለፈዉ ዓመት መጨረሻ የልዕለ ኃያልዋ አገር የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ሳምንት ሲቀራቸዉ ባለፈዉ ሐምሌ ነበር በድንገት የተለቀቁት። ከእስር መዉጣታቸዉ ይታወቃል። ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ አርብ ደግሞ በሌለችበት የተከሰሰችዉ ወጣት የድረ-ገጽ ፀሐፊናን ጨምሮ ሌሎች አራት ተከሳሾች መከላከል ሳያስፈልጋቸው ነበር፤ ክሳቸዉ የተነሳዉ። ባለፈዉ ረቡዕ ያስቻለዉ የፊደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእስር ላይ የነበረዉን የመጨረሻዉን የዞን ዘጠኝ የድረ -ገጽ ፀሐፊ በ20ሽ ብር ዋስ ከእስር አሰናብቶአል። የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት CPJ፤ የ2015 ዓለማቀፍን የፕሬስ ነጻነት ተሸላሚ ያደረጋቸዉ ወጣት ፀሐፍትና ጋዜጠኞች ከእስር እንዲፈቱ ጥሪ ሲያስተላልፍ መቆየቱ ይታወሳል። ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት፤ የፀረ ሽብሩ አተገባበር የመወያያ ርዕሳችን ነዉ።

በዚህ ርዕስ ላይ የሚወያዩልን፤ አቶ ጌታቸዉ ረዳ የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር፤ አቶ ያሪድ ኃይለማርያም የዓለም ዓቀፍ የሕግ ባለሞያ፤ አቶ ተማም አባቡልጎ ጠበቃ፤ እንዲሁም ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማ ናቸዉ። ሙሉ ዉይይቱን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።