1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውዝግብና ውጥረት በ COMESA ላይ የፈጠረው ችግር፧

ማክሰኞ፣ ኅዳር 5 1999

21 መንግሥታት በአባልነት የሚገኙበት የምሥራቃዊውና የደቡባዊው አፍሪቃ አህጉር የጋራ ገበያ ማኅበር፧ የተባበረ፧ ጠንካራ፧ አንድ-ወጥ የቀረጥ ሥርዓት ለማስተዋወቅ ያለው እቅድ፧ በአካባቢዎች ውጥረትና በውስጣዊ ውዝግቦች ሳቢያ እየተፋለሰ ነው።

https://p.dw.com/p/E0dM
ልጆች ወታደሮች፧ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ፧
ልጆች ወታደሮች፧ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ፧ምስል AP
ይህ ደግሞ፧ የአፍሪቃን አገሮች በሰፊው ባቀፈው የንግድ ማኅበር፧ የታሰበው የኤኮኖሚ ኅብረት እንዳይፈጠር፧ ባለሥልጣናት እንዳሉት፧ ደንቃራ ነው የሚሆነው። .....ተክሌ የኋላ........
የምሥራቃዊውና የደቡባዊው አፍሪቃ የጋራ ገበያ (COMESA) አባል አገሮች መሪዎች ነገ ጂቡቲ ላይ በ 11 ኛው ጉባዔ ተሰባስበው ለምምከር በዝግጅት ላይ እንዳሉ፧ ሥፍር ቁጥር የሌለው ችግር የተጋረጠባቸው እንደመሆኑ መጠን፧ በአካባቢያዊው ንግድ ላይ አለመረጋጋት መከሠቱን ሆኗል ያመላከተው።
በቀላሉ የፀጥታ መደፍረስ ሊያጋጥማት የምትችለው ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክም ሆነች፧ አሁን ከውስጣዊ ትርምስ ባሻገር፧ ለአካባቢያዊ ጦርነት ሰበብ እንዳትሆን የምታሠጋው ሶማልያ፧ የማኅበሩን አባላት አላሰሰቡም ማለት አይቻልም። የ COMESA ዋና ጸሐፊ Erastus Mwencha ፧ በአካባቢው፧ አለመረጋጋት አለ። ይህ ደግሞ ንግድንና ነጻ እንቅሥቃሴን ይገታል ነው ያሉት። እ ጎ አ ከ 1991 ዓ ም አንስቶ ከትርምስ ያልተላቀቀችው ሶማልያ የ«ኮሜሳ« አባል አይደለችም። ይሁንና ደካማውን የሽግግር መንግሥት በመፈታተን ላይ ያሉት የሸሪያ ፍርድ ቤቶች ኅብረት ሚሊሺያ ጦረኞች፧ በአካባቢ አገሮች፧ የውክልና ጦርነት በማስነሣት፧ እ ጎ አ እስከ 2008 ዓ ም፧ ትክክለኛ የጋራ የሆነ የቀረጥ ሥርዓት ለማስተዋወቅ የተነደፈው እቅድ እንዳይሠራ ሊያደናቅፉ ይችላሉ ነው የሚባለው።
በንዑሷ የቀይ ባህር አዋሳኝ ሀገር በጂቡቲ የተጠቀሰው የምሥራቃዊውና የደቡባዊው አፍሪቃ የንግድ ቀጣና አካባቢያዊ አገሮች መሪዎች ከመሰብሰባቸው በፊት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ ተሰብስበው፧ ውዝግብ ላጋጠማቸው መንግሥታት መፍትኄውን በማፈላለጉ ረገድ ይመክራሉ። ይሁንና ከአንዳንድ ባለሥልጣባት እንደሚሰማው፧ ሰላም በማስገኛ ሐሳብ ረገድ፧ መንግሥታቱ እንደተከፋፈሉ ናቸው።
«ኮሜሣ« 400 ሚልዮን ሰዎች፧ ማለትም የአፍሪቃ ክፍለ ዓለም ገሚሱ ህዝብ የሚኖርበት አካባቢ ነው። በአጠቃላይ የአባል አገሮቹ ያልተጣራ ብሔራዊ ገቢም 170 ቢልዮን ዶላር(132ቢልዮን ዩውሮ) ነው።
የንግድ ቀጣናው ማኅበር ዋና ጸሐፊ ኤራስተስ ምዌንቻ እንዳብራሩት፧ የጋረቅ ቀረጥ ስምምነት ከ 2008 ዓ ም አንስቶ ተግባራዊ መሆን ይኖርበታል። ለዚህም ዝግጅት ተደርጓል። ይሁንና አባል አገሮች፧ አንዳንድ ደኖችን ማስተዋወቅ ይኖርባቸው፧ ወደፊት ለመራመድ የግምጃ ቤት አያያዛቸውንም ማስተካከል ይጠበቅባቸውል።
ከውጭው ዓለም ጋር ንግድን ለማሻሻል፧ ኮሜሳ፧ ከአውሮፓው ኅብረት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሳመር ይሻል። በአሁኑ ጊዜ በሁለቱ ዐበይት የንግድ ቀጣናዎች መካከል፧ 22 ቢልዮን ዶላር የሚያስወጣ የንግድ ልውውጥ እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል።
ነገ፧ ጂቡቲ ላይ የመሪዎች ጉባዔ ከመካሄዱ በፊት፧ በዋዜማው፧ ነጋዴዎችንና ፖለቲከኞችን ጭምር ያሳተፈ፧ ከ 500 በላይ ልዑካን የተገኙበት ስብሰባ በመምከር ላይ ነው። በነገው ጉባዔ፧ ቢያንስ ሰባት ርእሳነ-ብሔር ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
እ ጎ አ በ 1993 ዓ ም የተመሠረተው ኮሜሳ፧ 21 አገሮችን በአባልነት ያቀፈ ሲሆን፧ አባሳቱም፧ አንጎላ፧ ቡሩንዲ፧ ኮሞሮ ደሴቶች፧ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ፧ ጂቡቲ፧ ግብፅ፧ ሱዳን፧ ኢትዮጵያ ኤርትራ፧ ኬንያ፧ ሊቢያ፧ ማደጋስካር፧ ማላዊ ሞሪሸስ፧ ናይጀሪያ፧ ዩጋንዳ፧ ሩዋንዳ ሲሸልስ፧ እስዋዚላንድ፧ ዛምቢያና ዝምባብዌ ናቸው።