1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወጣት ሴቶች እና የሚያሰጋቸው ፆታዊ ጥቃት

ዓርብ፣ ነሐሴ 8 2007

ወጣት ሴቶች በመንገድ ፣ በአካባቢያቸው እና በአጠቃላይ በዙሪያቸው ምን ያህል ደህንነት ይሰማቸዋል? የወጣት ሴቶች ፆታዊ ጥቃት ስጋት የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት ርዕሳችን ነው።

https://p.dw.com/p/1GEPI
Gewalt gegen Frauen Symbol
ምስል picture-alliance/dpa

ወጣት ሴቶችና የፆታዊ ጥቃት ስጋት

ሴቶች በተለይ ደግሞ ወጣት ልጃ ገረዶች ለፆታዊ ጥቃት የተጋለጡ ናቸው። ጥቃቱ መንገድ ላይ ከሚደርስባቸው ለከፋ አንስቶ እስከ መደብደብ እና መደፈር ሊደርስ ይችላል። ሴቶች ራሳቸውን ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል ስለሚያስችሉዋቸው መብቶች ይበልጥ እየተገነዘቡ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ድረስ ፆታዊ ጥቃት ሲደርስባቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው የማያውቁ ወይም በሴቶች ላይ ጥቃት ሲፈፀም እያዩ እንዳላየ የሚያልፉ ጥቂቶች አይደሉም።
ሴቶች ውጭ አምሽተው ብቻቸውን ወደ ቤታቸው እንዳይመለሱ ከሚያደርጉቸው ምክንያቶች አንዱ ጎዳና ላይ ሊገጥማቸው የሚችለው የፆታዊ ጥቃት ፍርሃቻ እንደሆነ ይናገራሉ። ይህ ግን ጥቃቶች ከመሸ ብቻ ይፈፀማሉ ማለት አይደለም፣ በቀንም ይፈፀማሉ። ሴቶች፣ በተለይ ወጣቶች በሚኖሩበት አካባቢ ወይም በዙሪያቸው ምን ያህል ደህንነት እንደሚሰማቸው እና ምን ያህል ሳይሰጉ እንደሚንቀሳቀሱ በጠየቅንበት ወቅት የሐዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ወጣት ደራርቱ አየለ ፤ በራሷ ላይ የገጠማት ጥቃት ባይኖርም ከጓደኞቿ ጋር የዮኒቨርስቱ ትምህርቷን የምትከታተልበት ሆሳዕና ከተማ ውስጥ የገጠማቸውን ገልፃልናለች።

Demonstration gegen Gewalt an Frauen
ምስል picture-alliance/dpa

እንደ ደራርቱ ዓይነት ገጠመኝ ያላቸው ወጣቶች ጥቂቶች አይደሉም። ከነዚህ አንዷ የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ክሓሲት አፅብኻም ናት። ክሓሲት አመሸች ቢባል እስከ ሁለት ሰዓት ድረስ ነው። እየተለከፉ እና እየተሰደቡ ዝም ብለው የሚያልፉት ሴቶች ቢከሱ ምን ያህል የሕግ ከለላ ያገኛሉ? የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች የሴቶች ማህበር አላል እና የሴቶች መብት ተሟጋች ሰመሃን ጌታቸው፤የመንገድ ላይ ለከፋን ሕጉ እንዴት ይመለከተዋል ለሚለው እና ሌሎች ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥታናለች።
ዘገባውን በድምፅም ያገኙታል።


ልደት አበበ
አርያም ተክሌ