1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኮሮና እና ኮቪድ፤ ኢትዮጵያ ተዘናጋች?

እሑድ፣ ታኅሣሥ 11 2013

ከኮቪድ ሕመም ከ20 ቀናት በኋላ ያገገሙት አቶ ፍሰሐ ወልደገብረኤል በኢትዮጵያውያን ዘንድ የታዘቡት መዘናጋት ያሳስባቸዋል። "የሚጠነቀቀውን ሰው እንደ ፈሪ" የማየት ዝንባሌ መኖሩን የሚናገሩት አቶ ፍሰሐ "ጉንፋን ነው፤ ምን ታካብዳለህ?" የሚል አስተያየት ሰምተዋል።የአቶ ፍሰሐ ሥጋት በሕክምና ዶክተሮችና የማሕበረሰብ ጤና ባለሙያዎች ዘንድም ይታያል

https://p.dw.com/p/3myl2
Coronavirus in Äthiopien Addis Ababa Mann mit Schutzmaske
ምስል AFP/M. Tewelde

እንወያይ፦ኮሮና እና ኮቪድ፤ ኢትዮጵያ ተዘናጋች?

የኮቪድ ሕሙማን በአዲስ አበባ በጽኑ ሕሙማን ክፍሎች ገብቶ ለመታከም እና ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሣሪያዎች ለማግኘት ወረፋ መጠበቅ ጀምረዋል። ጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚገቡ እና ቬንትሌተር ተብሎ የሚታወቀውን ለአተነፋፈስ እገዛ የሚያደርግ ሰው ሰራሽ መሣሪያ የሚጠቀሙ ሕሙማን የመዳን ዕድል እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ ደግሞ ለኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል።

የጤና ምኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በኢትዮጵያ "በየቀኑ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ወደ ሕክምና ማዕከል ከሚገቡት ታማሚዎች ውስጥ በአማካይ 305 የሚሆኑት ጽኑ ሕክምና ክፍል ይገኛሉ።" ከ40 እስከ 45 የሚሆኑት ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ የሚጠቀሙ ናቸው።

ወረርሽኙ በጤና ተቋማት ላይ የሚያሳድረው ጫና እየበረታ ቢመጣም የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የመጠቀም ባህል ግን በአዲስ አበባም ይሁን በክልል ከተሞች እየቀነሰ መምጣቱን ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የጤና ሚኒስቴር ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ኮሮና ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ ባሉት አምስት ወራት በምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው የሚረጋገጥ ሰዎች ብዙ የነበሩ ቢሆንም አብዛኞቹ ወጣቶች ነበሩ። አሁን ግን ዕድሜያቸው የገፋ፤ ቀድሞም ሌላ ሕመም የነበረባቸው ሰዎች ላይ በመድረሱ በጽኑ የመታመም ዕድላቸው ከፍ ብሏል።

ከኮቪድ ሕመም ያገገሙት አቶ ፍሰሐ ወልደገብርኤል፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ጤና ባለሙያው አቶ ትዝ አለኝ ተስፋዬ እና በድሬዳዋ የሕክምና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር አቤል መልካሙ የተሳተፉበት የሳምንቱ ውይይት ኢትዮጵያ እና ዜጎቿ ተዘናግተዋልን? ሲል ይጠይቃል።

ሙሉ ውይይቱን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ